ABOUT US

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በመንግስት ኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ሥርዓት ውስጥ የመሪነት ሚና በመጫወት ፤ በመንግስትና በሕዝቡ መካከል ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንፎርሜሽን ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ዓለምአቀፋዊና  ሀገራዊ እንድሁም ክልላዊ በጎ ገጽታ በመገንባት ጉልህ ሚና የሚጫወት ነዉ፡፡

ዓላማ፣

በተቋሙ የማህበራዊ ሚዲያ አሰራሮችን በማጠናከር፣ ይዘቶችን በማዘጋጀትና በማሰራጨት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ውጤቶችን በመከታተልና በመተንተን፣ ግንኙነቶችን በማጠናከር የማህበራዊ ሚዲያ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ነው፡፡

ተልዕኮ፤

በመንግስት ተቋማት ወጥ፣ ተናባቢ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የመረጃና ተግባቦት እንዲሁም የመንግስት ኮሙኒኬሽ አመራርና ሥርዐት በመዘርጋት ለሁሉም ዜጎች የመንግስት መረጃን የማግኘት ዕድል በመፈጠር፤የመንግሥት አጀንዳዎች ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፤ የኮሙኒኬሽን ተግባራት በጠንካራ፣የምርምር፣ ሙያዊ ብቃትና ፈጠራ ማጎልበት፡፡

ራዕይ፣

የዜጎችን መንግስታዊ የመረጃ ፍላጎት የሚያሟላ ተኣማኒ፣ ውጤታማ እና ቀድሞ ተንባይ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት በ2022 እውን ማድረግ፤

ዕሴቶች፣

  • ግልጽነትና ክፍት፣
  • ብዙኃኒነትና እኩልነት፣
  • ተደራሽነት፣ወቅታዊነትና ምላሽ ሰጭነት፣
  • ሙያዊ ብቃትና ፈጠራ፣
  • .  ተኣማንነትና ትክክለኛነት፣

የቢሮ ኃላፊዎች እና የሥራ ክፍላቸው

አቶ የሺዋስ ዓለሙ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት፣በዲጂታል ሚዲያና የመንግስት መረጃ አደረጃጀት የተሻለ ተቋም የመሆን ዓላማ ያለዉ ተቋም ነዉ።በቢሮድስካስቲ ሚዲያ፣ በህትመትም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ(new media) በመታገዝ ተዓማኒ የሆኑ መረጃዎችን በመስጠት የመምራት፣ የማስተማርን የማንቃት ኃላፊነት የሥራችን አካል ነው። በአጠቃላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መዋቅር በሁለንተናዊነቱ ሲታይ የመንግስት አፍ በመሆን የቃለ ቀባይነት ሚናን በማሳደግ በፍጥነት፣በዉጤታማንና  በጥራት የመስራት ኃላፊነት ይጠበቅበታል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የክልሉን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ለማስተዋወቅ የተቻለውን ሁሉ ጥረት እያደረገ ነው። ክልላችን  በተፈጥሮ ሀብቱ፣ ባህላዊ እና ማህበራዊ  እሴቱ የደረጀ ክልል ነዉ። በ ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ከተመዘገቡት  የባዮስፌር ሪዘርቭስ ውስጥ ሁለቱ በዚህ ክልል ውስጥ ይገኛሉ። የካፋና የሸካ ባዮስፈር ሪዘርቮች።እንደ ኦሞ፣ ባሮ እና ጎጀብ ያሉ ትላልቅ ወንዞች በክልሉ ይገኛሉ። ብዙ ዞኖች አመታዊ የዝናብ መጠን ከፍተኛ ፤አንዳንዴም እስከ 2200 ሚ.ሜ. ይደርሳል። በክልሉ በዋናነት እንደ ቡና፣ ሻይ፣ ቅመማ ቅመም፣ ማር፣ የእንስሳት እርባታ እና እንዲሁም እንደ ወርቅና ድንጋይ ከሰል ያሉ ማዕድናት እና ሌሎች በርካታ የሰብል ምርቶችን ይመረታል። ክልሉ ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክን እና አየኦሞ ብሄራዊ ፓርክን በዉስጡ ይዟል።

ዶ/ር መስፍን ወዳጆ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመንግስት መረጃና ዲጂታል ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ

የመንግስት መረጃ ማዕከልና ዲጅታል ሚዲያ አስተዳደር ዘርፍ በምክትል ቢሮ ኃላፊ የሚመራ ሲሆን የአሰራር ስርአትን ከክልል እሰከታችኛው መዋቅር (በዞን፤ወረዳ/ ከተማ አስተዳደር ደረጃ) በመዘርጋት፤ የክልሉ አጠቃላይ የመንግስት መረጃዎችን በአንድ ማዕከል ተደራሽ ለማድረግ የመረጃ ቋት (database) በማደራጀት፣ ቤተ-መጽሐፍትና ዲረ-ገጽ በመገንባት በመረጃ ነጻነት አዋጅ መሠረት ለተገልጋዮች በተቀላጠፈ መልኩ ለማድረስ ይሰራል፡፡ በሰክተሩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችና ዲረ-ገጽ ላይ የሚጫኑ መረጃዎች ይዘታቸውና የአጻጻፍና አቀራረፅ ስልታቸው ወቅታዊ፤ ሳቢና አንባቢን ወይም ተመልካችን የሚጋብዙ፤ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና በተገልጋዮች ተፈላጊ ሆነው እንዲጎበኙ የሚስችሉ አሠራሮችን በመቅረጽና ተደራሽ በማድረግ የሚሠራ ዘርፍ ነው፡፡ እንዲሁም ዘርፉ በማስታወቂያና ህትመት ስራዎች ዙሪያ ለሚሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት በመስጠት የዘመነ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ለመገንባት ዓላማ ይዞ የሚሠራ ዘርፍ ነው፡፡

Government Information Center and Digital Media Administration Division is headed by the Deputy Head of the Bureau, and it establishes a communication system from the Region to the lower level (at the zonal, woreda / town administration level). It works to make the Region’s Government information available to a single center by organizing database, building library and website and providing it to customers in accordance with the Freedom of Information Proclamation. The division works hard to make contents and styles of information posted on the social media pages and websites of the Government Communications Affairs Bureau of the Region up-to date, attractive and accurate to the readers and viewers. It is a division that specializes in designing and making services that meet the quality standards and make them accessible to consumers. It is also aimed at building an up-to-date information management system by issuing certificates to organizations and individuals involved in advertising and publishing

ወ/ሮ በረከት ኢዮብ፣ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ

የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዘርፍ በሁለት ዋና ዳየይሬክቶሬቶች የተዋቀረ ሲሆን እነሱም የሚዲያ ሞኒተርንግ ጥናትና ምርምር እንድሁም አቅም ግንባታ እና ኮሙኒከሽንና ሚዲያ ግኑኝነት ናቸው፡፡ዘርፉየቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ መነሻ ያደረገ የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ዕቅድ በማዘጋጀትና በማስተባበር በበላይነት ይመራል፣ ይገመግማል፣ የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፣ በሚሰጠዉ ግብረ-መልስ መሠረት ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፣ በዚህም ለብሄራዊ መግባባትና  ለገጽታ ግንባታ ልዩ ልዩ የህትመት ውጤቶችን በማዘጋጀትና በማሰራጨት ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል ፡፡የሚድያ ፎረም እና ታላላቅ ሁነቶች ይመራል ያሰተባብራል  ወቅታዊ ጉዳዮችን በመለየት ወቅታዊ የኮሙኒኬሽን አጀንዳ ይቀርጻል ፡፡ ክልሉን የሚገልጹ ብራነዲነግ ሰራዎች ይሰራል የክልሉን ዕምቅ ሃብት በማስተዋወቅ እና በመሸጥ ሁሉ አቀፍ እድገት ሊያሳሊጥ የሚችል አቅም አንዲፈጠር በአጽንኦት ይሰራል፡፡ወቅታዊ መረጃዎችን ለማድረስ ዜና፣ ፕሮግራም፣ ዶክመንተሪ፣ የአቋም መግለጫ አዘጋጅቶ በሚዲያ በማስተላለፍ ተደራሽ የማድረግ ስራ ያከናውናል፡፡የመንግስት ኢንፎርሜሽን አገልገሎት ጥራትን ለማሳደግ የተለያዩ ኤግዚብሽን ስራዎችን በማዘጋጀት ለህዝብ ለዕይታ ያቀርባል በገጽ ለገጽ በፓናል ውይይት መረጃዎችን የማስረጽ ስራ ይሰራል ፡፡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከባለድርሻ አካላትና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር የሚያደርጓቸውን ውይይቶች፣ የትብብር ስምምነቶችና የሚካሄዱ የሥራ ጉብኝቶችን የተመለከቱ መረጃዎች በጽሁፍ፣ በድምጽና በምስል እንዲያዙ በማድረግ፣ እንደአስፈላጊነቱም ለሚዲያ ዘገባና ፕሮግራም በግብአትነትና በማጣቀሻነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ ስራ ከናውናል ፡፡ በወቅታዊና አገራዊ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ፕሬስ ሪሊዝ፣ ፕሬስ ኮንፍረንስ እና የመንግስት አቋም መግለጫ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲዘጋጅ በማድረግ እና በቃለ ምልልስ የመንግስት መረጃ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በማስተባበር፣ በህዝብና በሚዲያው ውስጥ የፈጠረውን አወንታዊና አሉታዊ አዝማሚያ ተከታትሎ በመተንተን ለመረጃ ግብአትነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግና፣ አፈጻጸሙንም የመከታተል ስራዎችን ያከናውናል ፡፡ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች የክልሉን የልማት እንቅስቃሴዎችንና ስኬቶችን በአካል ተገኝተው እንዲጎበኙ እንዲዘግቡ የሚድያ ጥቆማ ይሰጣል ያስተባብራል ፡፡ የሕዝብ አስተያየት ጥናትና ምርምር አገልግሎት ተደራሽነት ማሳደግ  የሚዲያ ሞኒተሪንግ መረጃዎች ትንተና እና አዝማሚያ ዳሰሳ ጥናት ስራዎችን ይፈጽማል፡፡የጥናትና ምርምር ተግባራትን በማቀድ፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ የአሰራር ስርአት በመዘርጋትና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር እንዲሁም የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በአፈፃፀም ወቅት የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ የህዝብ አመለካከትና የሚዲና ኮሙኒኬሽን ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ፤የመፍትሔ ሀሳብ ያመነጫል፡፡ በየወቅቱ ያለውን እድገት እና ተጨባጭ ሁኔታን ያገናዘበ ብቃትና ብስለት ያለው ሳይንሳዊና ዘመን ተሻጋሪ ሃሳቦችን በማፍለቅ፣ ክልላዊ የኢንፎርሜሽንናየሚዲያ ጥናትና ምርምር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም የሴክተሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም የሚያጎለብቱ የአሰራር መመሪያዎችን፤ ደንቦችን በማዘጋጀት፤ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና ተሞክሮዎችን በመቀመርና በማስፋት የሴክተሩን ውጤታማነት የማሳደግ ስራ ያከናውናል::