የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በመጀመሪያ አጀንዳነት የተመለከተዉ የቀረቡለትን የኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን ነዉ። በዚህም ካላቸዉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፣ ከሚያስገኙት ስራ ዕድል አኳያ ከ1 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 36 የግብርና እና 3 የኢንዱስትሪ በአጠቃላይ 39 የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ከተወያየ በኃላ ወደ ሥራ እንዲገቡ ወስኗል። ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳነት የተመለከተዉ የቀረቡለትን ረቂቅ ደንቦች ነዉ። በዚህም የማዕድንና…

Read More

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በተመለከተ

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግበ የምክር ቤቱ አባላት ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ለታሃድሶ ኮሚሽንን እና ለሽግግር ፍትህም መሰል ድጋፍ መደረግ አለበት፡፡ ከዚህ ቀደም ከነበሩ ኮሚሽኖች ትምህርት በመውሰድ አሁን ያሉ እድሎችን መጠቀም ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ መንግስት እንደ አስፈጻሚ አካል የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

Read More

‹‹የገዢ ትርክት ዕሳቤ በመደመር መንገድ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው››፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የገዢ ትርክት ዕሳቤ በመደመር መንገድ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛው ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄ ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽና ማብራሪ፤ ገዢ ትርክት አሰባሳቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ -ክፍል ሁለት

– ሰላምና ደህንነትን በተመለከተ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፡፡ ጦርነትን በተግባር እናውቀዋለን፤ አንፈልገውም፡፡ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው፡፡ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፡፡ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ነገር ግን የትኛውም አካል በኃይል እና ጥላቻ መጠፋፋትን እንጂ ዓላማውን ማሳካት አይችልም፡፡ ሰከን ብሎ ማሳብ ይገባል፡፡ ሃሳብ አልባ ትግል…

Read More

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፎርሙ እጅ አጠር ዜጎችን የሚጎዳ እንዳይሆን ከፍተኛ የድጎማ በጀት መያዙን አስታውቀዋል፡፡ ከደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዙ የመረጃ ክፍቶችን በማጥራት ማሻሻያው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡ የዋጋ ግሽበት የዓለም ሀገራትን በተለያየ ደረጃ እየፈተነ እንደሚገኝ…

Read More

ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶች ለአቅመ ደካማ ዜጎች ተላልፈዋል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መንግስት ባለሐብቶችን በማስተባበር ባከናወነው ስራ ባለፉት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶችን በመስራት እና በማደስ ለአቅመ ደካማ ዜጎች መተላለፋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ኢትዮጵያ ውስጥ ለአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት ሰርቶ መስጠት ልምምድ ያደረገ የግል ባለሐብት እየተፈጠረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በዚህ ተግባር ውስጥ የተሳተፉ ባለሐብቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና…

Read More

በሽፍትነት ወደ ሥልጣን የሚመጡ ሰዎች የኢኮኖሚ ለውጥ አያመጡም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰላምን በመተመለከተ በሰጡት ምላሽ ዴሞክራሲን በመገንባት ሂደት የሰላም ማጣት ዋጋ ያስከፍላል ብለዋል፡፡ ሰላም በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ሰው ለሚያገኘው ጥቅም የማይመጣጠን ዋጋን የማይከፍል አመዛዛኝ ፍጡር ስለሆነ ሰላም ከሁሉም በላይ እንደሚያስፈልገን መዝኖ መያዝ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሰላም ግን አንድ ወገን ስለፈለገው ብቻ የሚሳካ እንዳልሆነ እና ሁሉም ለሰላም ዝግጁ…

Read More