በህገ-ወጥ ጦር መሳሪያ እና ኮንትሮባንድ ዝውውር የተጠረጠሩ 23 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ከጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ሃያ ቀናት በስድስቱም ዞኖች ከሚገኙ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ እና የክትትል ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል የተለያዩ ህገወጥ ቁሳቁሶችን እንዲያዝ አድርገዋል። በዚሁ መሠረት የጦር መሳሪያዎች፤ቡና፤ኮሮሪማ፤ ናፍጣ፤ቤንዝል፤ሀሰተኛ ገንዘብ፤ለወንጀል መፈጸምና ወጣቶችን ወደ ወንጀል የሚገፋፋ የሺሻ ዕቃዎች እና ደን ውጤቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ…
