ኢትዮጵያ እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በመሰረተ ልማት ግንባታ ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክሩ ገለጹ
ኢትዮጵያ እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በመሰረተ ልማት ግንባታ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ከእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የኮርፖሬት ፀሐፊ ሰር ሼራርድ ካውፐር-ኮልስ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል። ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በባንኩ መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ነው። በውይይቱ ወቅት በዋናነት በትብብር ሊከናወኑ…
