ባንኩ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ። የባንኩ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የአብሥራ ከበደ÷ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ባንኩ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በእውቀትና ክህሎት የሚመሩ ጠንካራ ኢንተርፕራይዞች እንዲፈጠሩ ተከታታይ ሥልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ገልጸው፤…
