
የዳውሮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ውስጥ ከሚገኙ ስድስት ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ 10 ወረዳዎችና አራት የከተማ አስተዳደሮችን በውስጡ ያቀፈ ነው።
በዞኑ ውስጥ ለህዝብ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የሚሰሩ ብዙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይገኛሉ። ከነዚህም አንዱ የሆነው በህዝቡ ጉልበት፣ ዕውቀትና ገንዘብ ተቋቁሞ በመንግሥት መሸፈን ያልተቻሉ የልማት ክፍተቶችን ለመሸፈን እየሰራ ያለውን የዳውሮ ልማት ማህበር (ዳልማ) በዛሬው ዝግጅታችን ለመቃኘት እንሞክራለን።
የዳውሮ ልማት ማህበር (ዳልማ) ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን ፍቃድ የተሰጠውና ከ1993 ዓ/ም ጀምሮ በስራ ላይ የሚገኝ አንጋፋ ሀገር በቀል የልማት ድርጅት ነው።
ማህበሩ የዞኑ ህዝብ ያለበትን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በማጥናትና በመለየት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትንና መሠረተ ልማት አውታሮችን በተጠናከረ መልኩ ለመዘርጋት ህብረተሰቡን፣ አባላትንና በአከባቢው የሚገኘውን ሀብት በማስተባበር በልማት ስራ ላይ በማዋል የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚሰራ ተቋም ነው።
የማህበሩ አባላት፣ ደጋፊዎች፣ አጋር ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በሚገኘው ሀብት መንግስት መድረስ የማይችልባቸው የበጎና የተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ በዛብህ ገልጸዋል።
ዳልማ ግዙፍ የልማት ስራዎችን ማከናወን የቻለ ትልቅ የህዝብ ባለውለታ ድርጅት መሆኑን ያወሱት የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ተጠናቅቆ ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት ላይ ካሉ ጥቅቱን በአኃዝ ለመግለጽ ያህል፦
በትምህርት ዘርፍ 64 ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የአቅም ግንባታ ስራ፣ እንዲሁም ግብዓት የማሟላት ስራ መሠራቱን፤ በጤና ልማት ሥራዎች 22 የጤና ኬላ ግንባታና ማስፋፊያ፣ የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል የእናቶችና ህፃናት ህክምና ክፍል እንዲሁም ግብዓት የማሟላት ስራ መሠራቱን በንጹሕ መጠጥ ውሀ አቅርቦት 74 ቦኖዎች፣ በግብርናና አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ 16 የእንስሳት ጤና ክሊኒክ ግንባታ የተሰሩ መሠረተ ልማቶችን በእንክብካቤ ለመጠቀም ግንዛቤ የማስጨበጥ የአቅም ግንባታ ስራዎች መሠራቱን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
የማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ለተለያዩ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ድጋፍ ማድረጉን የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ በአጠቃላይ ከ400 ሚለየን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መገንባቱን እና ሰፊ የዞኑን የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አክለዋል።
ይሁን እንጂ ልማት ማህበሩ በፊት ባለው አቅም ልክ እንዳይንቀሳቀስ ማነቆዎች መኖራቸውንም አልሸሸጉም።
የሀብት እጥረት መኖሩ፣ ከአባላት የተሰበሰበው ሀብት በጊዜ ያለመተላለፍ፣የተቋማዊ ማኔጅመንት ክፍተት፣ በሀገርቱና በዓለም ደረጃ የተከሰተው ጦርነት ምክንያት ረጂ ደርጅት መቀነስ/ውስንነት እና የተከናወኑ ተግባራትን ለአባላቱ ግልጽ ያለማድረግና የሚዲያ አጠቃቀም ችግሮች እንደሆኑ ኃላፊው ጠቅሰዋል።
ከላይ የተዘረዘሩትን ማነቆዎችን በመፍታት ዘርፈ ብዙ የሆነውን የማህበረሰብ ልማት ለማረጋገጥ ማህበሩ ከዞኑ መንግስት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ቀላል የማይባሉ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ አንስተዋል።
ከዞኑ መንግስት አካላትና ህዝብ ተወካዮች ጋር በመሆን በቀጣይ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች የዳውሮ ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤትን በማቋቋም ከአጠቃላይ አባላት ከየማህበራዊ መሠረት ከ500 ሚለዮን .ብር በላይ ለማሰባሰብ በንቅናቄው ግብ ጥሎ በማስተባበር ላይ ይገኛል።
በበዞኑ ውስጥ፣ ከዞኑ ወጪ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በቴፒና ሌሎች ከተሞች ነባር አባላትን የማነቃቃትና አድስ አባላትን የማፍራት ስራ በሰፊው እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በባህል፣ ታርክና ቋንቋ ልማትና ቅርስ ጥበቃ ስራ ላይ በ98 ሚለየን ብር በ5025 ካ.ሜ ቦታ ላይ ክልሉን የሚመጥን ትልቅ የባህል አዳራሽ ግንባታ እየተካሄደ ሲሆን የፕሮጀክቱ አፈጻጸም 23% እና ስትራክቸር ስራው 71% ደርሷል ነው የተባለው።
አንድ የማህበረሰብ ት/ቤት “ሂዶታ” በመከፈቱ ባለፉት ሦስት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ከተፈተኑት በ2014 ዓ/ም 100%፣ በ2015 ዓ/ም 95% እና በ2016 ዓ/ም 100% ተፈታኞች ውጤት በማምጣት ወደ ዩንቨረሲቲ መግባት መቻሉንና 33 ተማሪዎች በአሁኑ ሰዓት በዳልማ ወጪ በት/ቤቱ እየተማሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በ2016 ዓ/ም በማረቃ ወረዳ በሞዴል ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጃፓን ኢምባሲ ጋር በመተባበር 1 ብሎክ ባለ 4 የመማሪያ ክፍል እና ሽንት ቤት ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ጨምረው አብራርተዋል ።
በማሪ ማንሳ ወረዳ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ከግልመር ኦፍ ሆፍ ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጀት ጋር በመሆን በስድስት ት/ቤቶች በ21 ሚለየን ብር ወጪ ለተለያዩ አግልግሎት የሚውል ህንፃና ግብዓትን የማሟላት ተግባር መከናወኑን አብራርተዋል።
Ripple effect ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመሆን በሁለት ወረዳዎች በአከባቢ ጥበቃና በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚገኙ 1870 የማህበረሰብ ክፍሎችን በድለባ በቁጠባና በጠባብ ማሳ ላይ ምርታማነትን ከመጨመር አንፃር በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
ከስራ ዕድል ፈጠራ አንጻር በማዕድን ልማት ስራ የድንጋይ ከሰል ለማምረት ቦታውን በመረከብ የምርት ፍቃድ ተወስዶ ወደ ማምረት ለመሸጋገር ዝግጅት ላይ መሆኑን አንስተዋል።
ከስራ ዕድል ፈጠራ በተጨማሪ ገቢን ለማመንጨት ብሎም በከተማው ቱርዝምን ለማነቃቃት እንግዳ ማረፊያ የሚሆን 12 ክፍል ሎጅ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
በመጨረሻም ልማት ማህበሩ ከገባበት ችግር ውስጥ በመውጣት እንደገና እንድንሰራራ ያገዘውን የክልልና የዞኑ መንግስት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አቶ ሙሉጌታ አመስግነዋል።
ልማት ማህበሩ በህዝብ ለህዝብ የተቋቋመ በመንግሥት መሸፈን የማይቻሉ የህዝብን የመልማት ፍላጎትን በመለየት የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጉልበት፣ ዕውቀትና ገንዘብን በማስተባበር የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በመሆኑ የሁሉንም ቅንጅትና ደጋፊን ይሻል የዝግጅት ክፍሉ መልዕክት ነው።
በጌታሁን ግርማ

ጥረትና እንቅስቃሰዉን በጣም እያመሠገኑኩ።። ዳዉሮ ልማት ማህበር በዳዉሮ ዞን ከተቋቋመበት ጀምሮ ይህንን ነዉ የማይባል ተግባራቶችን ስሰራም ስተገበርም ቆይቷል, የተለያዩ ሬጅ ድርጅቶች ማለትም ገሌመር ሆፕ፥ስንድ ካዉ,ሪፕል እፈክትና መሰል ደጋፊ ደረጅቶች በዳዉሮ ልማት ማ/ሪ በኩል ብዙ የመልካም አሰ/ር ችግሮችን መላሽ ስሰጥ ቆይቷል ይሁን እንጅ በተፈጠረዉ ችግርም ይሁን በአፈጣጠም ጉድለት በወል ባይታወቅም እንደኔ ጌለመሪ ሆፕ ዓይነት ፕሮጀክትን ለቆ ሰወጣ በጣም አዝንያለዉ, ይህ በዙ ምዕራፎችን ይዘጋል በዙ ልማቶችን ያሳጣል , ለዝህ ዋነናዉ ችግሪ ለፕሮጀክቱ የምመለከተዉ አካል ትኩረት ያለመሰጠት ነዉ ብዬ ነዉ ምያሰበዉ,ስለሆነም ያለፈ ዉሃ አይቀዳም የምመጣዉ እንጅ,አሁን ባለዉ ሁነታ መሠሪት ያለባቸዉ ፥መደጋገፈ ያለባቸዉ በትዉልድ መደጋገፈ ያለባቸዉኝ የተኛዉም መሰዋትነት ከፈለን ዛሬ ላይ እንደ ጭላንጭል አየታዬ ያለዉ ህዶታ ት/ት ቤት የዳዉሮ ባህል ማዕከል ጉዳይ ለማጠነቀቅና ቀጣይ ለዳዉሮ ዕጣ ፈንታ የምወሰን የዳዉሮ ልማት ማ/ር ለማስቀጠል የተለያዩ ፕሮጀክቶች እንድደገፉ የተለያዩ መጻጻፎች እንደ ቀድሞ ረጅ ተቋማት በማፈላለግና የተጀመረዉ የትዉልድ አንድነትን ከዉጭም ከዉስጥ አንድነት በማጠናከር በንሰራ ትናንት በጀማርዉ የታዩት ድሎችና አዳድስ ተማክሮችን በመቀመር ዳዉሮን ለትዉልድ ምቹና ዘመን አሻጋር ትዉልድ መፈጠር እንችላለን።።።።።መልካም ጊዜ
በአንድ አከባቢ ያለዉ የመልማት ፍላጎት ሊሟላ የሚችለዉ የሁሉም የተቀናጀ ትብብርና ቅንጅት እንደመሆኑ መጠን የዳዉሮ ልማት ማህበር ታሪካዉ አመጣጡ ረጅም ቢሆንም የሰሜን ኦሞ ዞን መበታተን ቦሃላ በአዲስ መልክ በ1993 ዓ.ም በዋናነት በዞኑ የሚገኙ ማህበረሰቦች; ከዞኑ ዉጭ ያሉ የዞኑ ተወላጅ ና ተባባሪ ግለሰቦች ገልበት; ገንዘብና ዕዉቀት በማስተባበር እና የተለያዩ አገራዊና አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች የሚገኘዉን ድጋፍ በዞኑ ዉስጥ በመንግስት ሊሸፈኑ ያልቻል የልማት ሥራዎችን ለማስተባበር የተቋቋመ አገር በቀል የልማት ድርጅት እንደሆነ በዚህም እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ መሠረታዊ የተባለዉ የአደረጃጀት ሥራዎች ለምሳሌ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በዞኑ ዋና ፅ/ቤትና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችን (በአምስቱ ወረዳዎች በጂማና በአ/አበባ) በመክፈት በአሠራር መመሪያ በሰዉ ሀይል በጽ/ቤና በፅ/ቤቶች ቁሳቁሶችን በማሟላት ጠንካራ የአሠራር ሥርዓት ተበጅቶለት በርካታ አባላትን በማፍራት መሠረታዊ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን በዚሁም ከአለም አቀፍ እርዳታ ድርጅት(ግሊመርኦፍ ሆፕ) በተገኘወ ድጋፍ የጌንዶ ባቾና የጉማሪ ኮቾ ጤና ኬላ እንዲሁም ዋካ መልስኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሁለት የመማሪ ብሎክ እና መፀዳጃ ግንባታ በማከናወን ፕሮጀክቶችን የማስፈፀም አቅም ያለዉ ተቋም መሆኑን በማስመስከር ከዛ ቦሃላ ከግሊመር ጋር በመሆኑ በርካታ የልማት ሥራዎችን ሠርቶ የዞኑ ሕ/ብ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል።
ይሁን እንጂ በርግጥ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ስለልማት ማህበሩ እንቅስቃሴ በቂ መረጃ ባይኖረኝም መንገራገጮች እንደነበረዉና በሚፈለገዉ ፍጥነት ባለመጓዙ አሁን ይህንን ችግር ቀርፎ ልማት ማህበሩ ን በማጠናከር የተቋቋመበትን አለማ ለማሳካት ከዞን ዉጭ ያሉርንጫፎችን መልሶ ለማጠናከር/ለማደራጀት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ጥሩ ናቸዉ በርቱ ያስብል።
በዚሁ ላይ ያለኝ አስተያየት ከዞን ዉጭ ያለዉን ለማጠናከር የሚደረገዉ እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ ቀደም ስል በ5 ወረዳዎች የተደራጁ ቅርጫፍ ፅ/ቤቶችና በአዳዲስ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያለዉ ሥራ እና የዋናዉ ፅ/ቤት በአደረጃጀትና የሥራ እንቅስቃሴ (ፋይናንሻል ና ፊዚካል እንቅስቃሴ) ያሉበትን ደረጃ የተለያዩ ሜዴያዎችን በመጠቀም ለባለቤቱም ሆነ ለረጂ ድርጅቶች ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ በማስደገፍ ለጆሮዎቻቸዉ ማድረስ ቢቻል የማህበሩን አሠራር ግልፀጭነትና ጥንካሬዉን በማረጋገጥ የተሳትፎ መጠንን ከፍ ሊያደርገዉ ስለሚችል ይኸዉ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። በተለይም ልማትን ለመሥራት ገንዘብ ብቻ ለማሰባሰብ ሳይሆን የዞኑን ልማት ለማፋጠን የሠለጠነ የሰዉ ሀይልን የማሰባሰብና በማሰተባበር እያንዳንዱ የዞኑ ብሄርም ሆነ ተወላጅ እንዲሁም ተባባሪ ግለሰብ ባለሙያዎችን በመቅረብ ልምዳቸዉንና ዕዉቀታቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ትኩረት ቢሰጥበት ጥሩ ነዉ የሚል አስተያየት አለኝ ከዚህ በተጨማሪ የዳዉሮ ልማት ማህበር አነሳስና አመጣጥ (ከቀድሞ ኩሎ ኮንታ ከሚባልበት ጊዜ ጀምሮ ያለዉ) በሚለዉ ሰፋ ያለ ጥናታዉ ፅሑፍ እንዲሁም የረጅምና (የተከለሰ ስትራቴጅክ) የአጭር ጊዜ እቅድ ዙሪያ ተዘጋጅቶ የንቅናቄ መድረኮች በሰፊዉ የማካሄዱ ሥራ ቅድሚያ ቢሰጠዉ እላለሁ።
ይህቺን ታክ አስተያየት እንድሰጥበት ምቹ ሁኔታ ለፈጠራችሁት ምስጋናዬ የላቀ ነወ።
ልማት የሁሉም የጋራ ጥረት ዉጤት በመሆኑ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የህብረተሰባችን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዕዉቀት በገንዘብና በጉልበት የበኩላችንን ሳንቆጥብ እንወጣ የሚል መልዕክቴ ነዉ።
እ/ር የልማቱ አስተባባሪዎችን; ተባባሪዎችንን የልማቱ ተጠቃሚ ሕብረተሰባችንን ይባርከዉ!
ግርማ ወርቁ ነኝ ከሚዳ ዘሎ(የመጀመሪያዉ የዳልማ ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበርኩ)