የሻይ ልማት ኢንሼቲቭን ተግባራትን በማጠናከር የገጠር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን በካፋ ዞን ገዋታ ወረዳ የቦጊንዳ የሻይ ችግኝ ዝግጅት ጣቢያ ከአካባቢው ለተወጣጡ አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ዓላማው የተዘጋጀውን የሻይ ቅጠል ችግኝን ከተከላ በፊት ከውጪው አየር ጋር በተገቢ ማላመድ፣ የመንከባከብና ከተላመደ በኃላ ወደ አርሶ አደሩ ማሳ በመውሰድ ለመትከል ከማሳ ልየታ እስከ ተከላና ምርት አሰባሰብ…
