Dawro Nationality
832,639
ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት
ታርጫ (Tarcha)
የዞኑ ዋና ከተማ
446,082 ሄ/ር
አጠቃላይ የቆዳ ስፋት
10 ወረዳ / 4 ከተማ
የአስተዳደር መዋቅር
የጀርባ ታሪክና መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ (Background & Geography)
የዳውሮ ዞን መዋቅር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ካሉ 6ቱ ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ በምድር ወገብ 6 ዲ.ስ፣59-7ዲ.ሴ 35 በሰሜን ላቲቲዩድ እና በ36ዲ.ሴ 6 ምስራቅ “ሎንግቲዩድ” መሥመሮች ውስጥ ይገኛል።
የወሰን አወሳሰን፦ በስተ ሰሜን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከጅማ ዞን ጋር፤ በስተ ምሥራቅ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካንባታ ጣንባሮ ዞኖች፤ በስተ ደቡብ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወላይታ ዞን፤ በስተ ምዕራብ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮንታ ዞን ያዋስኑታል። የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ስትሆን ከከተማዋ መነሻ አንስቶ በጅማ – አዲስ አበባ 505 ኪ/ሜ፣ በታርጫ-ሶዶ-አዲስ አበባ በኩል ደግሞ 534 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።
የህዝብ ሁኔታና ስነ-ህዝብ (Demographics)
አሁን ባለው የዞኑ ተጨባጭ መረጃ መሰረት አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 832,639 ሲሆን የዓመታዊ የሕዝብ ዕድገት መጠን 2.9% ነው። የህዝብ ስርጭት ስብጥር እንደሚከተለው ተዋቅሯል፡
| አካባቢ (Setting) | ወንድ (Male) | ሴት (Female) | ድምር (Total) |
|---|---|---|---|
| ከተማ (Urban) | 56,867 | 49,366 | 106,233 |
| ገጠር (Rural) | 367,904 | 358,502 | 726,406 |
| አጠቃላይ ድምር | 424,711 | 407,868 | 832,639 |
ዞኑ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የሚኖሩበት አካባቢ ሲሆን በዋናነት ነባሩ የዳውሮ ብሔረሰብ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። በተጨማሪም በኢሰራ ወረዳ ውስጥ በሰፈራ ፕሮግራም የመጡ የወላይታ እና ሀዲያ ብሔረሰብ ተወላጆች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በፍቅርና በሰላም አብረው ይኖራሉ።
መሬት አጠቃቀምና አየር ንብረት (Land Use & Climate)
ከባህር ጠለል በላይ ያለው ከፍታ ከ550 እስከ 2820 ሜትር ይደርሳል። የመልካዓ ምድሩ አቀማመጥ ወጣገባ፣ ኮረብታማና ተራራማ ነው። የስነ-ምህዳር ቀጠናው በሶስት ይከፈላል፡ 41% ወይናደጋ፣ 38% ቆላማ፣ እና 21% ደጋ ነው። ከፍተኛው ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከ1374.2 እስከ 2271.6 ሚ.ሜ ሲሆን፣ የሙቀት መጠን ከ15.1°C እስከ 27.5°C ይደርሳል።
የመሬት አጠቃቀም ስብጥር (446,082 ሄክታር)፦
- ቋሚና ዓመታዊ ሰብል፡ 290,002 ሄክታር (ከ65% በላይ)
- የተፈጥሮ ደን፡ 41,712 ሄክታር (9.35%) | አጠቃላይ የደን ሽፋን፡ 62,847 ሄክታር (14.08%)
- ለግጦሽ የተከለለ መሬት፡ 25,940 ሄክታር (5.81%)
- በውሃ የተሸፈነ፡ 7,695 ሄክታር
- ረግረጋማ መሬት፡ 317.16 ሄክታር
የማህበራዊ ልማት ተቋማት (Social Infrastructure)
ትምህርት ተቋማት (Education)
- 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡ 371
- 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡ 49
- ጠቅላላ ተማሪዎች (1-8)፡ 112,045
- ጠቅላላ ተማሪዎች (9-12)፡ 23,499
- ኮሌጆች፡ 6 የመንግስት እና 2 የግል
- ከፍተኛ ትምህርት፡ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ታርጫ ካምፓስ
ጤና ተቋማት (Healthcare)
- ጠቅላላ ሆስፒታል፡ 1
- የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፡ 3
- የጤና ጣቢያዎች ብዛት፡ 21

Dawro Nationality














