አልሚዎች የወሰዱት መሬት አሟጦ ማልማት ይጠበቅባቸዋል፦ ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በክልሉ ከሚያለሙ ባለሃብቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ክልላዊ ኢንቨስትመንት ፎረም በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የክልሉ መንግሥት ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ አጋጣሚዎችን በማመቻቸት ክልሉን የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ ይሰራል ብለዋል። አልሚዎች በወሰዱት መሬት በተሟላ አቅም ወደ ምርት መግባት እንዳለባቸውም ያሳሰቡት…
