ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶች ተፈራረሙ

Spread the love

ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በተለያዩ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነቶች ተፈራርመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ተወያይተዋል።

በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል፣ ሁለቱ መሪዎች በመከላከያ እና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

‎ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ(COP32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መሆናቸውን አመልክቷል።

‎በሌላ በኩል የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም “አሳን” (ASAN) እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ስምምነቶቹ እና የመግባቢያ ሰነዶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ ያጠናክራሉ እና ያስፋፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *