መንግስት በምግብ ራስን ለመቻል በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ተግባር የግብርናው ዘርፍ እና የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ፦ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በመደበኛ ፣ በማታና በተከታታይ የስልጠና ዘርፎች በደረጃ 4 ያሰለጠናቸውን 639 ተማሪዎች አስመረቀ። በ15ኛ ዙር የኮሌጁ የምረቃ ስነ ስርዓት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። አቶ ፍቅሬ አማን በንግግራቸው መንግስት በምግብ ራስን ለመቻል በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ተግባር ውስጥ የግብርና ዘርፍ እና…

Read More

ምዘናው የመምህራንና የትምህርት አመራር እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እንደሚያስችል ተገለጸ ።

‎ ‎ክልላዊ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና በይፋ ተጀምሯል። ‎ ‎ዛሬ በይፋ በተጀመረው ክልል አቀፍ ምዘና በሁሉም ደረጃዎች ከ7200 በላይ ነባር መምህራን ፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀዉን የፅሑፍ ምዘና እንደሚወስዱ ታውቋል። ‎ ‎ምዘናውን በይፋ ያስጀመሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ…

Read More

በመንገድ ልማት ዘርፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት ጥራት ላለው ስራ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ጋር በመቀናጀት በድልድይ እና መንገድ ልማት ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ የስልጠና መድረኩን…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?

ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት በዚህ አምድ አጠቃላይ የክልላችንን ገጽታ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የካፋና የዳዉሮ ዞኖችን አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳዩ ጽሁፎችን እንደየቅደምተከተላቸው ለውድ አንባቢዎቻችን አድርሰናል፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከክልላችን ዞኖች አንዱ የሆነውን የቤንች ሸኮ ዞንን እንቃኛለን፡፡ መልካም ንባብ! የቤንች ሸኮ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ከተዋቀሩ ስድስት ዞኖች አንዱ ነዉ፡፡ ዞኑ በስድስት ወረዳዎች፣ በአራት ከተማ አስተዳደሮች፣ በ137…

Read More

ከዓመታት አዙሪት መውጣት ያልቻልነው ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት ባለመቻላችን ነው፡- ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

ከዓመታት አዙሪት መውጣት ያልቻልነው ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት ባለመቻላችን ነው ሲሉ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፌደራል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን፣ የእድሜ ጠገብ ባለታሪክ የሆነችው ኢትዮጵያ በብዙ ውጣውረድ ውስጥ ማለፏን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ የገጠሟን ችግሮች ለመፍታት ህዝቡን በማሳተፍ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤…

Read More

የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን ደንብ በመረዳት ደንን ጠብቆ ከሚመረቱ ምርቶች የሚገኘውን ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለመሆን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።

በክልሉ ግብርና ቢሮ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ከናቡ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በቡና ልማትና ምርት አቅርቦት አፈጻጸም እና በአዲሱ የአውሮፓ ዩኒየን ደንብ(EUDR) ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የክልሉን ኢኮኖሚ ከሚመሩት ሰብሎች ግንባር ቀደሙ ቡና መሆኑን ገልጸዋል ።…

Read More

የኮ-ዋሽ ስትሪንግ ኮሚቴ ለ2018 በጀት አመት ለፕሮግራሙ ማስፈፃሚያ የሚሆን 50 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኮ-ዋሽ (COWASH)ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የክልሉ የኮ-ዋሽ ስትሪንግ ኮሚቴ የ2017 በጀት አመት የኮዋሽ ፕሮግራም የ10 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ምክክር ያደረገ ሲሆን የ2018 በጀት አመት የፕሮግራሙን ዕቅድ በገምግሞ 50 ሚሊዮን 106 ሺህ…

Read More

በተቀናጀ 2ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ ከ5 መቶ ሺህ 64 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሕጻናት የመከላከያ ክትባት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ

ክልላዊ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዞኑ ታርጫ ከተማ ተደርጓል። በዚህ ዘመቻ በክልሉ ሁሉም ቀበሌያት የተቀናጀ 2ኛ ዙር የልጅነት ልምሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ከግንቦት 22-25/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥም ተገልጿል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ቦጋለ እንደገለፁት ይህ የልጅነት ልምሻ በሽታ በብዛት ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት የሚታይ በሽታ በመሆኑ በአገር…

Read More

ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት ተመዝግበዋል

በኢትዮጵያ እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች የፋይዳ መታወቂያ አገልግሎት መመዝገባቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ኘሮግራም ገልጿል። በዚህ ዓመት መጨረሻም ከ20 እስከ 23 ሚሊዮን ለሚሆኑ ነዋሪዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራ የብሔራዊ መታወቂያ ኘሮግራም ምዝገባ ዳሬክተር አቶ ሄኖክ ጥላሁን ለኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ተናግረዋል። አሁን ላይ 5 ሺህ የሚሆኑ የምዝገባ መሳሪያዎችን በመጠቀም አገልግሎቱ እየተሰጠ መሆኑን አቶ…

Read More