መንግስት በምግብ ራስን ለመቻል በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ተግባር የግብርናው ዘርፍ እና የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ፦ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን

Spread the love

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በመደበኛ ፣ በማታና በተከታታይ የስልጠና ዘርፎች በደረጃ 4 ያሰለጠናቸውን 639 ተማሪዎች አስመረቀ።

በ15ኛ ዙር የኮሌጁ የምረቃ ስነ ስርዓት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ ክቡር አቶ ፍቅሬ አማን ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ፍቅሬ አማን በንግግራቸው መንግስት በምግብ ራስን ለመቻል በሚያደርገው ሁሉ አቀፍ ተግባር ውስጥ የግብርና ዘርፍ እና የግብርና ባለሙያዎች ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ፓርቲያችን ብልጽግ እና የለውጡ መንግስት ቁልፍ ዘርፎች አንዱ የግብርናው ዘርፍ መሆኑን ገልጸው ዘርፉን በሰው ሀይል ፣ በቴክኖሎጂና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

የግብርና ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በአመት 3 እና ከዚያ በላይ ወቅቶች ወደ ምርት የማስገባት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው በተለይም በሌማት ትሩፋት እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። እንደ ሀገር ምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ጥረት የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠኛ ኮሌጅ አዳዲስ የግብርና ባለሙያዎችና የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ ረገድ የራሱን ሚና እየተወጠ መሆኑን ገልጸዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍት በምረቃ መድረኩ እንደተናገሩት ሀገራችን ለግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ውጤታማነት የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ኮሌጁ ይህን ሀገራዊ ኃላፊነት ላለፉት 15 አመታት በትጋት ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል።

የአለምን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የግብርና ዘርፉ እምብርት ሆኗል ያሉት አቶ ሀብታሙ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀም ፣ የመስኖ ልማትን ማስፋት እና የግብርና ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ረገድ እንደ ሀገር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ተመራቂ ተማሪዎች በምትሄዱበት አካባቢ ሁሉ አርሶ አደሩን በማብቃት ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ የምግብ ዋስትናው እንዲረጋገጥ ኃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል።

የሚዛን ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ ዲን አቶ ካሳሁን ናይክን በመድረኩ እንደተናገሩት ተመራቂ ተማሪዎች የመጣችሁበት መንገድ ብዙ የህይወት ፈተና የበዛበት ፣ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፋችሁ ለዚህ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። አለም ዛሬ ላይ ተለዋዋጭና ውድድር የበዛባት ናት ያሉት ዲኑ ተመራቂ ተማሪዎችም በስራ አለም ተወዳዳሪና ተፍካካሪ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል።

ኮሌጁ በግብርናው ዘርፍ በመካከለኛ ዘርፍ በመደበኛ 6ሺ 433 ፣ በማታና በተከታታይ 11ሺ በድምሩ ከ17ሺ 433 በላይ ሰልጣኝ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማሰማራቱን ገልጸዋል።

በ3 አመት የኮሌጅ ቆይታቸው በየትምህርት ክፍሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ የዋንጫና የሰርተፍኬት ሽልማታቸውን ወ

መቀበላቸዉን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *