ክልላዊ የበጀት ድልድሉ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ መደረግ አለበት። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ክልላዊ የበጀት ድልድልና የገቢ እቅድ ላይ የባለድርሻ አካላት ምክክር በቦንጋ ከተማ እየካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ ከዚህ ቀደም ሲተገበር የነበረው ክልላዊ የበጀት ቀመርና ድልድል ለክልል ማዕከል የካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ አነስተኛ ሚና የነበረው በመሆኑ በቀጣይ ይህንን አሰራር በማሻሻል የ2018 በጀት…
