የፋይናንስ ስርዓት ጠንካራ፣ ግልፅ፣ ዘመናዊ እና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከክልል ቢሮዎች፣ ከዞን ፋይናንስ መምሪያዎች ፣ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር ሴክቶሪያል ጉባኤ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ክልላችን ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የፋይናንስ ስርዓትን ለማሻሻል መጠነ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል፤ብለው ለዚህም በየጊዜው የህግ ማዕቀፎችን በማሻሻል አሠራሮችን ወጥ ለማድረግ መሠራቱን አንስተዋል።

ወ/ሮ ወሰነች አክለው እንደ ሀገር የፋይንስ ሴክተር የተደራጀ እና የተሰናሰለ አሠራርን የሚጠይቅ በመሆኑ ሥርዓቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ውስብስብ አሰራሮችን ግልፅና ቀልጣፋ በማድረግ ጊዜና ጉልበት መቆጠብ ተችለዋል ብለዋል።

ፋይናንሱን በማስተዳደርና በመቆጣጠር በኩል የሚስተዋሉ ጉድለቶችና ክፍተቶችን ለማስተካከልና ለማዘመን የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ሪፎርም ፕሮግራሞች ተተግብረው ለውጦች ተመዝግበዋል ያሉት ኃላፊዋ መንግስት የግዥ ስርዓቱን በማዘመን በስራ ላይ ያሉትን አዋጆች በማሻሻል ከ 60% በላይ የሆነ የመንግስት ሀብት በወቅቱ ታቅዶ ግልፅ ውድድር በማድረግ አመርቂ ውጤቶችን ለማየት መቻሉን አስረድተዋል።

የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳይከሰት ከውስጥ ከሚገኘው ገቢ አቅምን ከድጎማ በጀት ጋር በማቀናጀት የተሻለ ስራ መሰራቱን ያነሱት ወ/ሮ ወሰነች የውስጥ ገቢ አቅሞቻችን በታቀደው መሠረት ሰብስቦ ለልማት እንዲውል ለማደረግ የተዘጋጀውን ደንብ በአግባቡ ተግብረናል ብለዋል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መንግስት ባደረገው አዋጅ ማሻሻያ መሠረት እንድሰሩ ተደርጓል ብለው ለአጠቃላይ አፈፃፀማችን የክልሉ የበላይ ኃላፊዎች ድጋፍና ቅንጅት የሚደነቅ ነው ብለዋል ኃላፊዋ።

በጉባኤው የክሉ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት የ 2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም በዝርዝር እየቀረበ ይገኛል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *