ክልሉ 21 ሺህ 877 ቶን ቅመማቅመም ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

21 ሺህ 877 ቶን ቅመማቅመም ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡ የክልሉ ቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር እና የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ልማትና ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ኮጁአብ÷ ክልሉ ለቅመማቅመም ልማት ቢያመችም የህግ ማዕቀፍ እና ወጥነት ያለው የግብይት ስርዓት አለመኖር ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም እንዳላስቻለ ገልጸዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ ክልላዊ የቅመማቅመም…

Read More

የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ልኡኳን ቡዱን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄደ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ ቡዱኑን ተቀብለው አነጋግረዋል። ልዑክ ቡዱኑ መርተው የመጡት የኩባ ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ ሲሆኑ የሁለቱን ሀገራት ለዘመናት የዘለቁ ቤተሰባዊነት የተላበሱ ግንኙነቶች የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርገዋል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ…

Read More

በተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣ ፓርቲ ነው ብልፅግና፡- ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

ብልፅግና ፓርቲ ከበርካታ ተግዳሮቶች ጋር እየታገለ መጠነ ሰፊ ለውጦችን ማምጣቱን የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትሩ ሁለተኛውን የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክቶ ከኢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ “ብልፅግና የሀሳብ ግልጽነት ያለው ፓርቲ እና ሀሳቡን ተግባራዊ በማድረግ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ለውጦችን ማምጣት የቻለ ነው” ብለዋል፡፡ ፓርቲው በአንደኛው መደበኛ ጉባኤው…

Read More

ባለፉት ዓመታት የስንዴ ምርታማነት ላይ በትኩረት በመሰራቱ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት ተችሏል፡- ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

ባለፉት ሥድስት ዓመታት የምርምር ተቋማትን በመጠቀም የስንዴ ምርታማነት ላይ በትኩረት በመሰራቱ ተጨባጭ እመርታዊ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ባለፉት ሥድስት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ሃሳባቸውን ያጋሩት የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፤ በስንዴ ልማት ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በመውጣት የምርምር ተቋማትን በመጠቀም በዕውቀት እና በእቅድ በተሰራው ስራ እመርታዊ ለውጥ መገኘቱን…

Read More

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በስድስት ወራት ውስጥ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አገኘ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢልዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ። የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር) የ2017 የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ በሰጡት ተቋሙ በስድስት ወራት ውስጥ በሺፒንግ አገልግሎት ከሁለት ሚልዮን ቶን በላይ ጭነት በባህር ማጓጓዙን ገልጸዋል። በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ከ654 ሺህ ቶን በላይ የገቢ እና ከ174 ሺህ ቶን…

Read More

ብልጽግና ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ አገራት የፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል። በዚህም የብሪክስ አባል ሀገር እህት ፓርቲ የሩሲያው ዩናይትድ ራሺያ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዲ .ኤ ሜዴቭዴቭ፣ የካዛኪስታኑ አማናት ፓርቲ እና የሀገሪቱ ፓርላማ የታችኛው ምክር ቤት አባል ሳማት ኑር ታተዛ፣ የኩባው ኮሚኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሜቴ አባል ዩዲ ሜርሴዲስ ኸርናንዴዝ፣ የቱርኬሚስታን ዲሞክራቲክ ፓርቲ…

Read More

ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከዛሬ ጀምሮ ያካሂዳል

ብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ‘ከቃል እስከ ባህል’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት ያካሂዳል። የፓርቲው ዓለም አቀፍና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት፤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው የፓርቲው 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎች ይወሰናሉ። በተጨማሪም ወሳኝ አቅጣጫዎች የሚተላለፍበት እንደሚሆን አመልክተዋል። በአዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ…

Read More

በዳዉሮ ዞን በዘንድሮ በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት 40 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የዞኑ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ልማት መምሪያ አስታወቀ

በዞኑ “የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ከጥር 22 ጀምሮ ለተከታታይ 45 ቀናት በዞኑ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ እንደሚካሄድም ተገልጿል። በዞኑ ከጪ ወረዳ የቺ ገዳ ንዑስ ተፋሰስ ዞናዊ በሆነው የማስጀመሪያ መርሀ ግብር የተገኙ አርሶአደሮች እንደሚሉት ባለፉት ዓመታት በለሙ የአፈርና ጥበቃ ሥራዎች አካባቢያቸው ተጠቃሚ መሆን ችሏል። በተለይ ቀበሌያቸው በአፈር አሲዳማነት የተጠቃ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚታየውን ችግር…

Read More

በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሮጀክቶች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው- ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች

በለውጡ ዓመታት ከቃል ወደ ተግባር መሸጋገር ያስቻሉ እና በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁ የአዲስ አበባ ከተማ ፕሮጀክቶች የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻሉ መሆናቸውን መመልከት እንደቻሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተናገሩ፡፡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎቹ ይህንን ያሉት ጉባኤውን በማስመልከት ባለፉት የለውጥ አመታት በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 3 ዓመታት የተከናወኑ ተጨባጭ…

Read More

ለማሻ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገት የድርሻቸውን እንደሚወጡ የማሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ

በማሻ ከተማ በእጅጉ የተቀዛቀዘው የንግድ እንቅስቃሴ ችግሩ ለይቶ እልባት እንዲሰጠው ተጠይቋል። በማሻ ከተማ አስተዳደር በመልካም አስተዳደርና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች ዙሪያ በመድረኩ የተሳተፉት አካላት በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት ለእኛ በመሆኑ የየድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል። የመድረኩ ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት በከተማው በክልል በፌደራልና በአካባቢው መንግስት በርካታ የመሠረተ ልማት ስራ ተሰርተው የሚታይ ለውጥ በመኖሩ ይህን አጠናክሮ…

Read More