

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በግማሽ ዓመቱ ከተለያዩ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢልዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር) የ2017 የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ በሰጡት ተቋሙ በስድስት ወራት ውስጥ በሺፒንግ አገልግሎት ከሁለት ሚልዮን ቶን በላይ ጭነት በባህር ማጓጓዙን ገልጸዋል።
በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ስርዓት ከ654 ሺህ ቶን በላይ የገቢ እና ከ174 ሺህ ቶን በላይ የወጪ ዕቃዎች ማስተናገዱን ጠቁመዋል።
በዚህም በስድስት ወራት ውስጥ ከሌሎች የገቢ ምንጮች 46 ነጥብ 7 ቢልዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ኤክስፖርት ላይ የተሻለ አፈጻጸምመመዝገቡን ጠቁመዋል።
በኮርፖሬት ስራዎችም ለረጅም ጊዜ ሳይዘጉ የቆዩ ሂሳቦችን መዝጋት መቻሉን ገልጸው፤ ያልተሰበሰቡ ሂሳቦችን ለመሰብሰብም የተሰራው ስራ ውጤት ማስገኘቱን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜ እየተጠናቀቁ ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቅሰው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩንም አስረድተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
