Trendings

Konta Zone

የኮንታ ዞን ፕሮፋይል – Konta Zone Profile

የኮንታ ዞን ፕሮፋይል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት

220,280

ጠቅላላ የሕዝብ ብዛት (2014)

አመያ (Amaya)

የዞኑ ዋና ከተማ

238,163 ሄክታር

አጠቃላይ የቆዳ ስፋት

62 ቀበሌያት

የአስተዳደር መዋቅር

ታሪካዊ አመጣጥና መልክዓ ምድራዊ ወሰን (History & Geography)

የኮንታ ዞን ወደ ዞን መዋቅር ከማደጉ በፊት በህዳር 1993 ዓ/ም የልዩ ወረዳነት ስልጣን ያገኘ ሲሆን፣ ወደ ሙሉ ዞን መዋቅር እውቅና አግኝቶ ያደገው በአዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መስራች ጉባኤ ላይ ህዳር 14 ቀን 2014 ዓ/ም ነው።

የሥነ-ፈለክ አቀማመጥ፦ ዞኑ በ 6.46′-7.26′ ሰሜን ላቲቲዩድ እና በ 36.32′-36.87′ ምስራቅ ሎንግቲዩድ መስመሮች ውስጥ ይገኛል።

የአጎራባች ወሰን መጋሪያዎች፦
  • በስተሰሜን፡ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን (ዴዶ እና ማንቾ ወረዳዎች)
  • በስተምዕራብ፡ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ ዞን (ጨታ፣ ዴቻ፣ ጠሎ እና አዲዮ ወረዳዎች)
  • በስተምሥራቅ፡ ከዳውሮ ዞን (ታርጫ ዙሪያ፣ ቶጫ እና ኢሰራ ወረዳዎች)
  • በስተደቡብ፡ ከደቡብ ኦሞ ዞን (ሰሊማጎ ወረዳ)
  • በስተደቡብ ምሥራቅ፡ ከጎፋ ዞን (መሎኮዛ ወረዳ)

ስነ-ህዝብ ሁኔታ (Demographics & Population Dynamics)

የህዝብ ቁጥር ትንበያ መረጃ መሰረት በ2014 ዓ/ም የዞኑ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 220,280 (ወንድ 108,649፣ ሴት 111,631) ነው። ዓመታዊ የህዝብ እድገት መጠኑ 2.9% ሲሆን፣ አማካይ የቤተሰብ አባላት ቁጥር 4.9 እንደሆነ ይገመታል።

የዕድሜ መዋቅር ስብጥር፦ በአምራች የእድሜ ክልል (ከ15-64 ዓመት) ውስጥ የሚገኘው የህዝብ ክፍል 50.9% (112,122) ሲሆን፣ አምራች ባልሆነ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ደግሞ 49.1% (108,157) ነው።

የከተማ እና ገጠር ነዋሪዎች ስብጥር፡

ቀጠና ወንድ (Male) ሴት (Female) ድምር (Total) ድርሻ (%)
የገጠር ህዝብ 91,935 93,155 185,090 84.02%
የከተማ ህዝብ 17,101 18,099 35,190 15.9%

የመሬት አጠቃቀምና አግሮ-ኢኮሎጂ (Land Use & Climate)

የዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 238,163 ሄክታር ሲሆን የመሬት አቀማመጡ 38.5% ተራራማ33.5% ተዳፋታማ እና 28% ሜዳማ ስነ-ቅርጽ አለው። ከባህር ወለል በላይ ያለው ከፍታ ከ790 ሜትር እስከ 2,750 ሜትር ይደርሳል።

የአየር ንብረት ቀጠናዎች፦ ወይናደጋ 54%፣ ቆላ 40% እና ደጋማ ክፍል 6% ይሸፍናል። ዞኑ የበልግና የመኸር ዝናብ ተጠቃሚ ሲሆን ዓመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ 1,745 ሚ.ሜ (ከ1,200 – 2,290 ሚ.ሜ) ይደርሳል። አማካይ የሙቀት መጠኑ 25.5°C ነው።

ዝርዝር የመሬት አጠቃቀም ስብጥር (ሄክታር)፦

የመሬት አይነት ስፋት (በሄክታር) አጠቃላይ ምድብ / ሽፋን (%)
የቋሚና ዓመታዊ ሰብሎች መሬት 99,326.76 ሄ/ር የእርሻ መሬት ሽፋን (58.4%)
ጠቅላላ የደን የተሸፈነ ክፍል (ተፈጥሮ፣ ግልና ማህበራት) 107,450.09 ሄ/ር የደን ሽፋን (46.1%)
በቁጥቋጦ የተሸፈነ መሬት 16,115.7 ሄ/ር ቁጥቋጦማ ቀጠና
ወደፊት ሊለማ የሚችል መሬት 14,068.99 ሄ/ር የልማት እምቅ አቅም
በግንባታ፣ በውሃ፣ በግጦሽና በረግረግ የተያዘ 10,518.46 ሄ/ር ሌሎች መሬቶች

ብሔራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶችና ማህበራዊ ልማት (Mega Projects & Social Sector)

የኮንታ ዞን በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ግዙፍ ስራዎች የሚከናወኑበት ስትራቴጂካዊ ቀጠና ነው፡

ቁልፍ ሀገራዊ ልማቶች፦
  • በሀገሪቱ በግዝፈቱ 2ኛ የሆነው የኮይሻ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፓወር ፕሮጀክት ግንባታ በዞኑ ውስጥ ይገኛል።
  • የታላቁ የ“ገበታ ለሀገር” የኮይሻ ፕሮጀክት የቱሪዝምና ልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑበት ይገኛል።

የጤና ተቋማት አውታር

  • 1 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • 5 ዘመናዊ ጤና ጣቢያዎች
  • 55 የጤና ኬላዎች

የትምህርት ተደራሽነት

  • 70 ጠቅላላ ትምህርት ቤቶች (1ኛ እና 2ኛ ደረጃ)
  • 36,000+ በትምህርት ገበታ ላይ ያሉ ተማሪዎች

  Konta Nationality in Konta                   

Konta Nationality

Cultural Images Of Konta Nationality

Etcetera