Trendings

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በዲያስፖራው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ወኪሎች ከየባለድርሻ አካላቱ ሲያስመርጥ መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሰራት የተወከሉት ተመካካሪዎች በተዘጋጀላቸው ማረፊያ ቦታዎች እየገቡ የሚገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ተመካካሪዎች እጅግ መሠረታዊ በሆኑ እና በተለዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በጋራ ለመምከር ዕድሉን…

Read More

‎የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያ ዙር የኦንላይን ፈተና አሰጣጥ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የፈተና ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል። ‎ ‎የቢሮው ምክትል ሀላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ሀላፊ ደስታ ገነሜ(ዶ/ር) እንደገለፁት በክልሉ በ18 ፈተና ማዕከላት 17,458 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና እንደሚወስዱ ገልፀዋል። ‎ ‎ፈተናው በስድስት ዙር በ18 ማዕከላት እንደሚሰጥ የገለፁት ምክትል ሀላፊው…

Read More

የሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት ከምስል ጋር!

የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢንዱስትሪ እድገትን እና ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ የአምራች ዘርፉ እንቅስቃሴዎችን በንቃት መርተዋል፤ በዚህም የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ ያተኮረውን 4ኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በይፋ የከፈቱ ሲሆን፣ የወጣቶችን የስራ እድል ለማስፋፋትም በአዲስ ኣበባ የሚገኘውን የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ…

Read More

በምርጫ ክልል ደረጃ የድምፅ ማዳመር ሥራ እየተከናወነ ነው – ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በወቅታዊ የምርጫው ሂደት ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፣ በየምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ ቆጠራ ተጠናቅቆ ውጤት መለጠፉን እና አሁን ላይ በምርጫ ክልል ደረጃ የማዳመር ሥራ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ሰብሳቢዋ በመግለጫቸው እንዳብራሩት፣ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ዘግይተው የነበሩ የምርጫ ጣቢያዎችን የድምፅ ቆጠራ ሂደት ትናንት ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የተመዘገቡ…

Read More

እንደ ምርጫ ባሉ ወሳኝ ሀገራዊ ሂደቶች የመገናኛ ብዙኃን ሚና እጅግ የላቀ ነው – ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ

እንደ ምርጫ ባሉ ወሳኝ ሀገራዊ ሂደቶች የመገናኛ ብዙኃን ሚና እጅግ የላቀ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን “ለዲሞክራሲያዊ ምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል ርዕስ በጋራ ያዘጋጁት መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን…

Read More

የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብና መተንተን ወሳኝ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዘርፉ የተመለከቱት እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል። መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት…

Read More

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች ነው

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች መሆኑን የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ። ”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ነው። በመድረኩ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት…

Read More

ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል

ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል ሲል የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ምክንያታዊነት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደት እንዴት እየተቃኘ ነው? ምክንያታዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ ለሚከናወን የሰላም ግንባታ እና የምክክር ሂደት ዋነኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በተቋቋመበት የመመስረቻ አዋጅ ላይ ምክንያታዊነት ከሀገራዊ ምክክሩ መርሆዎች አንዱ ተደርጎ መደንገጉ…

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ግንባታና የአፍሪካ አቪየሽን ልህቀት ተምሳሌት ነው – ከፍተኛ አመራሮች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ግንባታ ጉልህ ሚናው ብሔራዊ ኩራትን ከመፍጠር ባለፈ የአፍሪካ አቪየሽን የልህቀት ተምሳሌት ነው አሉ የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በማስመልከት ከደንበኞችና አጋሮች ጋር የደንበኞች ተሞክሮ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመርሐ ግብሩ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ(ዶ/ር)፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው…

Read More

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበዋል፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ። የሰባተኛው ጠቅላላ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቋል። ዜጎች በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ የዲጂታል አማራጭና በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የመራጮች ምዝገባ አከናውነዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ…

Read More