የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥትና ፓርቲ ሥራ ኃላፊዎች በቴፒ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥትና የፓርቲ የሥራ ኃላፊዎች በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተመልክቷል።

አመራሮቹ በከተማው እየተገነባ ያለውን የ“መሶብ” አንድ ማዕከል አገልግሎት እና የክልል ተቋማት የቢሮ ህንጻ ግንባታ ሂደት በቦታው ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።

የ“መሶብ” አንድ ማዕከል አገልግሎት ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ ተገልጋዮች በአንድ ስፍራ በርካታ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህም የጊዜና የወጪ ቁጠባን ከማረጋገጡ ባሻገር ግልፅነትና ተጠያቂነትን በማጠናከር መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከሚኖረው ሚና በተጨማሪ ሙስናና አላስፈላጊ መጓተትን ለመቀነስም ጉልህ ሚና ይጫወታል።

በሌላ በኩል የክልል ተቋማት የቢሮ ህንጻ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ የመንግሥት ተቋማትን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ ለህዝብ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ያግዛል።

እንዲሁም የቢሮ መበታተንን በመቀነስ የሥራ ቅንጅትን በማጠናከር የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋትና የህዝብ እርካታን ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *