የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የአካባቢን ጸጋ መሰረት አድርጎ በመተግበሩ ውጤት እየተመዘገበ ነው::
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች የአካባቢን ጸጋ መሰረት በማድረግ ለሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተከናወኑ ሥራዎች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሎቹ የሥራ ሃላፊዎች እንደገለጹት መርሀ-ግብሩ የአካባቢን ፀጋ መሠረት ባደረገ መልኩ ተግባራዊ በመደረጉ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ ናቸው። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት ሀገራዊው የሌማት…
