የአቶ ተዘራ ወ/ማሪያም አጭር የሕይወት ታሪክ
አቶ ተዘራ ወ/ማሪያም ሱራ ከአባታቸው ከሃምሳ አለቃ ወ/ማሪያም ሱራ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ በላይነሽ ጮቤ በቀድሞው ከፋ ክፍለሀገር በኤላ አውራጃ በአመያ ከተማ በ1973 ዓ/ም ተወለዱ። ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የአንደኛ ደረጃ ትምርህታቸውን በአከባቢያቸው ተከታትለው የኮሌጁ ትምርህታቸውን በአርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመምህርነት ተመርቀው በኦሽካ ዴንቻ ፣በኮንታ ኮይሻ፣በጨበራ ሻሾ ፣በኮዳ ማጂ፣በገንጂ ገነት፣በመዳየጃ በማስተማር ሙያና በጪዳ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት…
