አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተመድ ዋና ጸሀፊ ልዩ ተወካይና ዩኤንሶም ሀላፊ ጋር ተወያዩ::

Spread the love

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይና በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ድጋፍ ተልዕኮ(ዩኤንሶም) ሀላፊ ካትሪዮና ላንግ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም አምባሳደር ታዬ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ቀጣይነት ያለው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

ካትሪዮና ላንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ያደረገችውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ የቀጣናውን ሰላም ለማረጋጋት በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *