


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመደበኛ እና ካፒታል በጀት ዕቅድ ላይ ከክልሉ ግብርና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት ጋር የበጀት ሰሚ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት አጠቃላይ ለ2017 በጀት ዓመት ለሰው ሃይል፣ ለመደበኛ ስራ ማስኬጃ እና ለካፒታል የሚሆን የበጀት ዕቅድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል፡፡
በየበጀት ዓመቱ የሚታቀዱ የመደበኛ እና ካፒታል በጀት ዕቅዶች ያለውን ውስን ሀብት መሠረት በማድረግ መታቀድ እንደለባቸው፣ የበጀት ዕቅድ ከተግባር ጋር የተጣጣመ መሆን እንደሚገባና ከበጀት ጣሪያ በላይ ሆነው የቀረቡ ዕቅዶች ማስተከካያ ሊደረግባቸው እንደሚገባ በውይይቱ ተነስተዋል፡፡
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ገልፀው እነዚህን የተጀመሩ ነባር የካፒታል ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ ግብርና ቢሮና ተጠሪ ተቋማቱ ክልሉ ያለውን አቅም በውል ተገንዝቦ በስራ ላይ ሊውል የሚችል የበጀት ዕቅድ በማዘጋጀት እና በመገምገም ወደ ሥራ ማስገባት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የልማት ዕቅድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን በቀለ በበኩላቸው የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ተሳቢ ባደረገ መልኩ ተቋማት የበጀት ዕቅድ ማቀድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ ተቋማቱ ወስደው ማስተከካል በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
