ውስን የሆነውን ሀብት እና ውድ ጊዜያችንን በአግባቡ ለመጠቀም ተግባራትን በቴክኖሎጂ አስደግፎ ማከናወን እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ አሳሰቡ።
የክልሉ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ የክልሉን የቪዲዮ ኮንፈራንስ አገልግሎት ይፋዊ ማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄዷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ለክልሉ መንግሥታዊ አገልግሎት ውጤታማነት ፋይዳው የላቀ ይሆናል ብለዋል። የቪዲዮ ኮንፈንስ አገልግሎቱ የመረጃ ልውውጥ ሂደትን የሚያቀላጥፍ ብሎም ጊዜ እና ሀብትን የሚቆጥብ ተመራጪ ቴክኖሎጂ መሆኑንም ኃላፊዋ…
