በክልሉ በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለማድረግና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ዲጂታል የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን በሚዛን አማን ከተማ በይፋ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማት ማናጅመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ከሚገኙ ብዘሀ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት…
