

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የዋና ኦዲቴር መስሪያ ቤትየመስሪያ ቤቱን አደረጃጀት በማጠናከር ዓለም አቀፍ መስፈርትን ያሟላ የኦዲት ስራ ለማከናወን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ዋና ኦዲተር አቶ አቶ አስራት አበበ ገልፀዋል።
ዋና ኦዲተሩ ይህንን የገለፁት ከፌዴራል ኦዲት መስሪያ ቤት በተሰጠ የስራ ግብረመልስ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ዉይይት ነዉ።
በዋና መስሪያ ቤቱ ነፃ፤ ገለልተኛና ቀልጣፋ የኦዲት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን የጠቆሙት አቶ አስራት የመስሪያ ቤቱን አደረጃጀት በማጠናከር ዓለም ዓቀፍ መስፈርት ያሟሉ የኦዲት ስራዎች ለማከናወን በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።
አዳዲስ የኦዲት አሰራሮችን ሥራ ላይ ማዋል፤ ወጥ የሆነ የኦዲት ስርዓት መከተል፤ ተጋላጭ ተቋማትን መለየት፤ የሰዉ ሀይል ማሟላት፤ አደረጃጀቱን ማጠናከርና ጠንካራ የኦዲት ድጋፍና ክትትል ስራዎችን ማከናወን የኦዲት ስራን ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸዉን ዋና ኦዲተሩ አብራርተዋል።
የመስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ኦዲተር አቶ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው የመስሪያ ቤቱን የኦዲት ሽፋን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዉ ለዚህም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ለባለሙያና ባለድርሻ አካላት የሚያስፈልጉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በወቅቱ መስጠት የሰዉ ሀይል ልማት ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍም ወሳኝ ተግባራት መሆናቸዉም ምክትል ዋና ኦዲተሩ መናገራቸዉን የመስሪያ ቤቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።
