በ18 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገነባ የዛን አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ::

Spread the love

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ የዛን የድልድይ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀመጥዋል።

የድልድይ ግንባታዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን የግንባታ አጠቃላይ ወጪ 18 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚፈጅ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

ከጃንቹ ወደ ጃንቹታ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚሰራው የዛን ወንዝ አነስተኛ ድልድይ ግንባታ በአካባቢዉ የሚመረተዉን ምርት ወደ ገበያ ለማድረስ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነዉ።

የደቡብ ቤንች ወረደ ዋና አስተዳደሪ አቶ ወልዱ ባጪ አካባቢው ከፍተኛ ምርት የሚመረትበት አካባቢ መሆኑን ጠቅሰው ይህ የሚገነባው የዛን ወንዝ ድልድይ በአካባቢው የሚስተዋለውን የመሠረተ ልማት ቸግር የሚቀርፍ በመሆኑ ክልሉ ለደረገው ድጋፍ ምሰጋና አቅርበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በመሠረተ ድንጋይ ባሰቀመጡበት ወቅት ደቡብ ቤንች ወረዳ እንደክል የሚሰጠውን ተልዕኮ ወስዶ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ እንዲሁም ትላልቅ የድልደይና የመንገድ ግንባታ በማከናወን ሞዴል ቀበሌ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ለሌሎች ወረዳዎች እንደተሞክሮ መቅረብ የሚችል መሆኑን በመናገር ወረዳው አሁን እያሳየ ያለውን መልካም አፈፃፀም አጠናክሮ ማስቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

ጠንክሮ የሰራ ሰው ይሸለማል ያሉት አቶ ማስረሻ የዚህም ማሳያ ዛሬ መሠረተ ድንጋይ የተቀመጠ የዛን ወንዝ ድልድይ ግንባታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግንባታው 3 ወር ከ15 ቀን ተሠርቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ፕሮግራም ላይ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የቤንች ሸኮ ዞን አመሮችና የደቡብ ቤንች ወረደ አመራሮች እና የጃንቹ ቀበሌ ህዝብ ተገኝቷል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *