


የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሚንኬሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ በተለያዬ አራት ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም በ15 ግለሰቦች ላይ በከባድ የማታለል ወንጀሎች በመፈፀም ክስ ተመስርቶበት በፖሊስ ሲፈለግ መቆየቱን ፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል።
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪውን በተገኘበት እንዲያዝ ከፍርድ ቤት መያዣ ጋር በመላካቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ እና የወንጀል ምርመራ ክትትል አባላት አሰማርቶ ግለሰቡን በመከታተል በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አመልክቷል፡፡
ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ለጥቂት ጊዜያት ሊደበቅ ይችል ይሆናል እንጂ ፈፅሞ ከህግ ሊያመልጥ እንደማይችል የግለሰቡ በቁጥጥር ስር መዋል ማሳያ ነው ያለው ፖሊስ ኮሚሽኑ ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሲውል ፤የቤት ፕላን፤የተለያዬ የባንክ ደብተሮች፤አንድ ላፕቶፕ፣የመኪና ቁልፍ እና የእጅ ስልኩ መያዙን ነው ፖሊስ ያመለከተው፡፡
በአንድ ክልል ወንጀል ፈፅሞ ሌላኛው ክልል በመሄድ መደበቅ እንደማይቻል እና ወንጀልን ለመከላከል ሁለቱ ክልሎች በጋራ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ተጠርጣሪዉን ለሸገር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስረክቧል፡፡
በመጨረሻም በክትትል ሂደቱ መረጃ እና ጥቆማ በመስጠትና ድጋፍ ላደረጋችሁ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የፖሊስ አባላት ምስጋናችንን እያቀረብን በቀጣይም ወንጀልን በጋራ መከላከል የሁሉም ኃላፊነትና ግዴታ በመሆኑ ህዝቡ ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
