በህይወት ክህሎት እና በስብዕና ግንባታ ወጣቱ ላይ በመሥራት ሀገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት እንደሚገባ ተገለጸ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ሌዊ እንደገለፁት ከሀገራችን የህዝብ ብዛት ከፍተኛ ቁጥር የሚዘው ወጣቶች መሆናቸውን ጠቁመው 1.2 ሚሊዮን ወጣቶች በክልሉ እንዳሉ ገልፀዋል።

ወጣቶች እምቅ ችሎታውን፣ ብሩህ አእምሮና የምርምርና የፈጠራ ዝንባሌን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ስብዕናቸው በተገቢው መቅረጽ የጥፋት ና አፍራሽ ነገሮች ውስጥ እንዳይገቡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ይገባል ብለዋል።

መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ችግሮች ለመፍታት፣ ተሳትፎ ና ተጠቃሚነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ና አደረጃጀቶችን በመፍጠር እየተሰራ መሆኑን የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ወጣቶች ከሌሎች ማህበረሰብ ጋር ካላቸው ከፍተኛ ድርሻ አንፃር በሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴ ፣ የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የላቀ ሚና መጫወት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባል ሲሉ ወ/ሮ ራሄል ተናግረዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለውን ወጣት ሊያስተናግድ የሚችል ጠንካራና የተረጋጋ ኢኮኖሚ መፍጠርና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ የወጣቶችን አደረጃጀት በሚገባ መጠቀም ምክትል የቢሮ ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ራሄል አክለውም የህይወት ክህሎት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ማርቆስ ጎቢ እንደገለፁት ወጣቶች ለሀገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ በመሆናቸው መንግስት ወጣቱን ይዞ የማይሻገረው ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል ።

ሀገራዊ ቱርፋቶችን ወደ አካባቢያችን በመለወጥ ረገድ ወጣቶች ሥራ ጠባቂ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እንደሚጠበቅ አቶ ማርቆስ ገልፀዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ሴቶች ፣ህፃናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ውቢቱ ገምታ እንደገለፁት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቱ እያደረገ ያለው አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል ።

ለወጣቶች የሚሰጡ አጫጭር ስልጠናዎች አቅም በፈቀደ እስከ ታችኛው መዋቅር የሚሰጥ መሆኑን ወ/ሮ ወቢቱ ጠቁመዋል ።

የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ሳምሶን ተሾመ በወጣቶች የህይወት ክህሎት ዙሪያ የስልጠና ሰነድ በማቅረብ ለሰልጣኞች አብራርተዋል ።

በስልጠናው የተሳተፉት በሰጡት አስተያየት ለህይወታችን ገንቢ የሆነ ለመለወጥ ጉዞ መነሻ የሚሆን ሀሳብ ያገኘንበት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን መስጠታቸዉን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

በሚዛን አማን ከተማ ካሉት ወጣቶች፣የስብዕና ልማት ቡድን መሪዎች፣ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *