




የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመርቋል ፡፡
ፊልሙ ትኩረቱን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ አድርጓል፡፡
ፊልሙን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰውኛ ፕሮዳክሽን እና ኢንተርቴይንመንት ጋር በመሆን በጋራ አዘጋጅተውታል።
በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዝግጅቱም ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢንጅነር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና እሳቤው “በትልቅ እናስባለን፤ ከትንሹ እንጀምራለን” በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዛሬ ላይ ሀገራችን ከዘርፉ ተጠቃሚ እንድትሆን ሀገር የሚያኮራ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል ማለታቸውን ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።
