በክልሉ በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለማድረግና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ::

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ዲጂታል የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን በሚዛን አማን ከተማ በይፋ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማት ማናጅመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ከሚገኙ ብዘሀ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት የሚያስችል የአሰራር ስረአት እንደክልል በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት በከተሞችን የሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶችን በዘመናዊ የአሰራር ስረአት በመዘረጋት እያንዳንዱን ፋይል ድጅታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህም በሃገራችን ዘመናዊ ከተሞችን ለመመስረት እንዲቻል የተጀመረውን ስራ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ያስችለዋል ያሉት አቶ ጫናቸው አሁን ላይ ስራው በሚዛን አማንና ቦንጋ ከተሞች ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም በተርጫና ቴፒ ከተሞች ላይ የዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ስረዓቱ እንደሚጀምር ገልጸዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም እንደተናገሩት በከተማዋ አሁን ላይ እያሳየች ያለውን ለውጥና ዕድገት የሚመጥን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ስረዓቱ መጀመሩ አበረታች እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በተለይ በማዘጋጃ ቤቶች ከዚህ ቀደም ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ህብረተሰቡን ለምሬት የሚዳርግና የመልካም አስተዳደር ችግር የበዙበት መሆኑንም አቶ ግሩም ገልጸዋል

አሁን ላይ በማዘጋጃ ቤቱ የተጀመረው ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ስረዓትም የህብረተሰቡን እርካታ በእጅጉ የሚያሳድግና ከዚህ በፊት ይነሱ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችንና ደካማ የመረጃ አያያዝ ስረዓትን የሚቀርፍ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፌዴራል ከተማና መሰረተልማት ሚኒስቴር የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትና የከተሞች ደረጃ ማዘመን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ታረቀኝ በበኩላቸው በሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ላይ ያሉ ማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጡትን አገልግሎቶች ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ በማድረግ የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሀገሪቱ በቅርቡ በ20ከተሞች ላይ ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ስረአት መጀመሩን የተናገሩት አቶ ታረቀኝ በክልሉ በሚዛን አማንና ቦንጋ ከተሞች የዘመናዊ ስረአቱ የማስጀመር ስራ እየተሰራ ነው መሆኑን ገልጸዋል

በተለይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ከተሞችን ለማዘመንና ለነዋሪዎች ምቹና ሳቢ የማድረግ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሚዛን አማን ከተማ ዋና ማዘጋጃ ቤት በተካሄደው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የፌዴራልና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊዎች የዞን አመራሮችን ጨምሮ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች መሳተፋቸዉን ደሬቴድ ሚዛን ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *