የኮንታ ልማት ማህበር 10 ሺህ ቶን የድንጋይ ከሰል ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ እየሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ።

በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ አስተዳደር የድንጋይ ከሰል ማምረት፣ የግብርናና ሌሎች ልማት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ ሥራ ኃላፊዎች ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነጋ አበራ የተፈጥሮ ሀብትን ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሲናውል አካባቢን በሚጠብቅና የተሻለ ገቢ በሚያስገኝ መልኩ መሆን እንደሚገባ ጠቁመው በኮንታ ልማት ማህበር ባለቤትነት እየተካሄደ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል የማምረት…

Read More

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ የታክስ አስተዳደርን ለመደገፍ የአምስት ዓመት ፕሮጀክት መቅረፁን ገለፀ::

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ በፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ የገቢዎች ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ÷ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2022ዓ.ም ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ተገንብቶ ሃገራዊ ወጪ በታክስ ገቢ ተሽፍኖ የማየት ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ይህንንም ራዕይ ከግብ ለማድረስ እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ዓለምዓቀፍ ተቋማት ጋር አብሮ መሥራት ትልቅ አቅም ይፈጥራል ያሉት ወ/ሮ ዓይናለም ሚኒስቴር…

Read More

በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻልና የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ተከናውኗል-አቶ አልማው ዘውዴ::

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት የተማሪዎች ውጤት መሻሻልና የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ በማድረግ ረገድ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘዉዴ ገልጸዋል። የ2016 በጀት ዓመት ክልላዊ የትምህርት ልማት ስራዎችን በሚመለከት የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ ሰጥቷል። በምክትል ርዕሰ…

Read More

በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮ-አሜሪካ የቢዝነስ እና የኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ::

ዋሽንግተን ዲ.ሲ.የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ኤምባሲ ከዋፋ ማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ-አሜሪካ ቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት ፎረም በዋሽንግተን ዲሲ አካሂዷል። የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚህ ጊዜ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የውጭ እና የውስጥ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ኢኮኖሚው እነዚህን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ አሁንም ዕድገት እያስመዘገበ ነው። የዚህ ዋነኛ ምክንያት ደግሞ በመንግስት እየተተገበረ ያለው መጠነ ሰፊ የሪፎርም ስራና በመሰረተ ልማቶች ላይ…

Read More

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ሰራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል:-የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ::

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የአራት ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት በዳመጡበት ወቅት ለኮሚሽኑ የምናደርጋቸው ድጋፎች በሃገር ግንባታ ስራችን ላይ አሻራ የምንጥልበት በመሆኑ አስፈላጊውን የቅንጅት ስራ በጋራ በመስራት ማገዝ ያለብንን የምናግዝ ይሆናል ብለዋል። የምክክር ኮሚሽኑ ሃላፊነትን በተላበሰ መልኩ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያገጥሙ ችግሮችን በመቋቋም የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ የስራቸውን…

Read More

ከባህላዊ ሐኪሞች ጋር በመተባበር ከ350 በላይ በሚሆኑ ለመድኃኒትነት በሚያገለግሉ እጽዋት ላይ ምርምር እያካሄደ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ::

የእንሰት እርሻን ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማስፋፋት እየሠራ ነው፡፡ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግርና የማህብረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ከለላው አዲሱ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከ350 በላይ እጽዋት ተለይተው በአንድ ማዕከል ውስጥ እንዲበዙና እንዲቀመጡ በማድረግ የምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ቡድን አዋቅሮ በየወረዳው ከሚገኙ የባህላዊ ሐኪሞች ጋር እጽዋትን ለይተው እንዲያሰባስቡና በአንድ ማዕከል ውስጥ…

Read More

ስታርት አፕ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር::

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ስታርትአፖች መበራከት እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ስታርትአፕን ለማበረታታት እየተሞከረ መሆኑ በመጥቀስ ቀጣይነት እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ተዘጋጅተው የሚመጡባቸው ምቹ መድረኮች እንዲኖሩ እየተሰራ ይገኛል የሚሉት ኃላፊው…

Read More

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው::

14ኛው ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡ ዳቢ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ በጉባዔው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡ በጉባኤው ከታዳሽ ኃይል እና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ…

Read More

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ማተኮር እንደሚገባ ተገለጸ::

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የልዑካን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን የተለያዩ የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ ከሚመለከታቸው ጋር የጋራ ውይይት አካሂደዋል። የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት በሥራ ክህሎት ላይ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችን በማስረጽ እንደ ሀገር የተጀመሩ ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ክልሉ ያለውን የአካባቢ ፀጋ በመለየትና በማልማት…

Read More

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሪፎርም ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ::

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሪፎርም ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ሕብረት ሥራ ኤጄንሲ ገለጸ። በአንድ ሺህ መሠረታዊ ማህበራት ላይ ሪፎርም እንደሚደረግ ተጠቁሟል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 2069 መሠረታዊ ማህበራትና 21 ዩኒየኖች ይገኛሉ። የሪፎርሙ ዓላማ የሕብረት ስራ ማህበራትን ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፣ የፋይናንስ አቅማቸውን ለማሳደግ፣ አሰራርን ለማሻሻልና የአባላትን…

Read More