ስታርት አፕ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር::

Spread the love

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ስታርትአፖች መበራከት እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ስታርትአፕን ለማበረታታት እየተሞከረ መሆኑ በመጥቀስ ቀጣይነት እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ተዘጋጅተው የሚመጡባቸው ምቹ መድረኮች እንዲኖሩ እየተሰራ ይገኛል የሚሉት ኃላፊው በቀጣይ ችግሮች የሚፈቱበት መድረክ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል፡፡

ስታርትአፕ ቢዝነስ እንደሀገር እያስተዋወቅን እንገኛለን የሚሉት አቶ ሰላምይሁን ፤የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስተካከልም እድል የሚፈጥር እንደሆነ ነው የገለጹት።

ከዚህ ቀደም የነበሩ ኤግዚቢሽኖች ሁሉም የሚሳተፉበት የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እንዲሁም ሶስተኛ ደረጃ በሚል በመከፋፈል እና የስራ ልምምድ እንዲኖራቸው እየተደረገ ይገኛል ብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *