


በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የልዑካን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን የተለያዩ የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ ከሚመለከታቸው ጋር የጋራ ውይይት አካሂደዋል።
የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት በሥራ ክህሎት ላይ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችን በማስረጽ እንደ ሀገር የተጀመሩ ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ክልሉ ያለውን የአካባቢ ፀጋ በመለየትና በማልማት አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር የሥራና ክህሎት ዘርፍ ትልቁን ሚና መጫወት አለብን ብለዋል።
በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ቁልፍ የሀገርን ችግር በመፍታት ረገድ በአዳዲስ ዕሳቢዎች ወደ ስራ መግባት የሚያስችል ሁኔታዎች በሚገባ መጠቀም ይገባል ሲሉ ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል
የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ማተኮር አማራጭ የሌለው መሆኑን አቶ ሰለሞን ገልፀዋል።
የማይክሮ ኢኮኖሚውን ችግር ተረድቶን በምንመራው ተቋም ወደ ተግባር ሊያስገባ የሚችል ሥራ መስራት ይገባል ሲሉ ሚኒስቴር ዴኤታው ጠቁመዋል ።
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከፍተኛ ባለሙያ በሥራና ክህሎት አዳዲስ እሳቤዎች ላይ የስልጠና ሰነድ ቀርቧል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛው ጋግያብ እንደገለፁት የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራው ልዑክ በቤንች ሸኮ የተለያዩ የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ተናግረዋል።
በድጋፍና ክትትላቸው ጠለቅ ያለ ከዞን እስከ አንድ ማዕከል የወረዱ ተግባራት የት መድረሳቸውን እና ችግሮችን ከመለየት ባለፈ በምን አግባብ መፈታት እንደሚችሉ በየደረጃው ግብረ መልስ ሰጥተውባቸዋል ሲሉ አቶ ግዛው ተናግረዋል።
በቀሪ ወራት በስራ ዕድል ፈጠራ ፣ በክህሎት ዘርፍ የተሻለ ሥራ መስራት የሚያስችል ሙያዊ ልምድ የወሰድንበት ድጋፋዊ ክትትልና በመጨረሻም የተሰጠ ስልጠና የግንዛቤ ክፍተትን የሚሞላ ነው ሲሉ የቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ሥራ፣ክህሎትና ኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በበኩላቸው ከጉብኝቱ ጎን ለጎን በተሰጠው ስልጠና ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር የተሳሰረ የክህሎትና የሥራ ዕድል ላይ ከኮሌጆች ጋር ተቀናጅቶ እንዴት መስራት እንዳለበት ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል ።
በክህሎት ዘርፍም አጫጭር ስልጠና እየሰጡ በቴክኖሎጂ ራስን ማብቃት እደሚገባ አቶ ሳሙኤል ጠቁመዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ መሰረት ከጉብኝት በኃላም በተሰጠው ስልጠና የተቋሙ ከወረዳ እስከ ዞን ያሉ አመራሮች ፣ባለሙያዎች ፣ በዞኑ ያሉየመንግስት ኮሌጅ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
