Trendings

በ18 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገነባ የዛን አነስተኛ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ ተቀመጠ::

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ የዛን የድልድይ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀመጥዋል። የድልድይ ግንባታዉ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን የግንባታ አጠቃላይ ወጪ 18 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚፈጅ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ከጃንቹ ወደ ጃንቹታ በሚወስደው መንገድ ላይ…

Read More

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት እንደሀገር እየታየ ያለዉን የስራ አጥነት ቁጥር በመቀነስ በኢኮኖሚው ዘርፍ የበኩሉን መወጣት የሚችል ትዉልድ የመቅረጽ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ::

የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት እንደሀገር እየታየ ያለዉን የስራ አጥነት ቁጥር በመቀነስ በኢኮኖሚው ዘርፍ የበኩሉን መወጣት የሚችል ትዉልድ የመቅረጽ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሳሰበ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከካፋ ዞን ስራ፣ ክህሎት፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ መምሪያ ጋር በመተባበር በአዲሱ ዘረመል እሳቤዎች ላይ ያተኮር ስልጠና በዞኑ ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሰጥቷል። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የደቡብ…

Read More

የህይወት ክህሎት እና የስብዕና ግንባታ ላይ በመሥራት ሀገር ተረካቢና ተተኪ ትውልድ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ በቴፒ ከተማ ለሚገኙ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የሸካ ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት በህይወት ክህሎት ዙሪያ ለታዳጊ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ለስብዕና ግንባታ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቴፒ ከተማ…

Read More

የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚከናወኑ ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር::

በክልሎችና በከተሞች የሥራ አጥ ቁጥርን ለመቀነስ የሚከናወኑ ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚደረገው ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ገለጹ። በአቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የሚኒስቴሩ የባለሙያዎች ቡድን በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ የተሰሩ ሥራዎችን ተዘዋውሮ እየተመለከተ ይገኛል። ቡድኑ በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊና አመራሮች ጋር…

Read More

በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት እየተደረገ ነው::

በፈረንሳይ ፓሪስ በሚካሄደው ኦሎምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ የላቀ ውጤት እንድታስመዘግብ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ከአማራ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በደሴ ከተማ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራትና ቅብብሎሽ መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡ እንደኮሚቴው አገላለጽ የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር በመጪው ሐምሌ ወር እንደሚካሄድም ታወቋል። በውድድሩ ኢትዮጵያ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘገብ ከወዲሁ የቅደመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ…

Read More

በክልሉ የአርብቶ አደሩን ህይወት የሚቀይሩ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸዉ እየተከናወኑ ነዉ፦አቶ ማስረሻ በላቸው::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤኒት ሻሻና በመኤኒት ጎልድያ ወረዳ በክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ በቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት(LLRP) የተሰሩ የልማት ሥራችን ጎብኝተዋል፡፡ ስትሪንግ ኮሚቴው በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒት ሻሻ ወረዳ ይሪኒ ቀበሌ ከይሪኒ ወንዝ በሶላር ሀይል ሰጭነት በተጠለፈ መስኖ የሚለማ የእንስሳት መኖ ልማት የጎበኘ…

Read More

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” የተሰኘ አዲስ አገልግሎት ይፋ አደረገ::

ተቋሙ ለአገልግሎት ያበቃው አዲሱ መተግበሪያ በቴሌብር ሱፐር አፕ ውስጥ የተካተተ ሲሆን በዋናነት ግብይት፣ ማህበራዊ ግንኙነትና መረጃ ልውውጥን በአንድ መተግበሪያ የያዘ ነው፡፡ አገልግሎቱን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ አዳዲሶቹ አገልግሎቶች የዲጂታል ህይወትን ከማቅለል ባለፈ እንደሀገር የተያዘውን የዲጂታል ገንዘብ ልውውጥ አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምዳል ብለዋል፡፡ “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” ደንበኞች እርስ በእርስ ወይም…

Read More

“ውጤታማ ለመሆን ዝቅ ብሎ መስራትና ችግሮችን መቋቋም ያስፈልጋል” – ወጣት አብዱልቃድር መኮ

ወጣት አብዱልቃድር መኮ ይባላል፡፡ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ ሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር መስራች እና የማህበሩ ሰብሳቢ ነው፡፡ ተወልዶ ያደገው ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ ነው፡፡ ከዚያም በኋላ ከልጅነት እስከ ወጣትነት በሚዛን አማን፣ ጅማ ተዘዋውሮ የቆየው አብዱልቃድር አሁን ኑሮውን ሙሉ በሙሉ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በማድረግ “ሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር” በማቋቋም የራሱን…

Read More

በረመዳን ጾም ወቅት የታየው የመረዳዳትና የመደጋገፍ መልካም እሴት በሌሎች ቀናትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የእምነቱ ተከታዮች ጠይቀዋል፡፡

ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች አንዱ የሆነዉ የኢድ አልፈጥር በዓል በመላው አለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር ታላቅ በዓል ነው፡፡ በዓሉም ከአንድ ወር የረመዳን ጾም ማብቂያን ተከትሎ በድምቀት የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም በሂጅራ አቆጣጠር ለ1 ሺህ 4 መቶ 45ኛ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል፡፡ ከእነዚህም በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ተገኝተን ያነጋገርናቸዉ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት አስተያየት ያለፈው የጾም…

Read More

በሚቀጥሉት 10 ቀናት ዝናብ ሰጭ ገጽታዎች በበልግ ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው ይቀጥላሉ::

በመጪዎቹ 10 ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በአብዛኛዎቹ የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ እየተጠናከሩ እንደሚቀፅሉ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡ በዚህ መሰረትም በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፤ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው ተጠቅሷል፡፡ በመሆኑም በበልግ አብቃይ አካባቢዎች በርካታ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ነው የተገለጸው፡፡ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብና በመካከለኛው…

Read More