“ውጤታማ ለመሆን ዝቅ ብሎ መስራትና ችግሮችን መቋቋም ያስፈልጋል” – ወጣት አብዱልቃድር መኮ

Spread the love

ወጣት አብዱልቃድር መኮ ይባላል፡፡ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ ሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር መስራች እና የማህበሩ ሰብሳቢ ነው፡፡ ተወልዶ ያደገው ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ ነው፡፡

ከዚያም በኋላ ከልጅነት እስከ ወጣትነት በሚዛን አማን፣ ጅማ ተዘዋውሮ የቆየው አብዱልቃድር አሁን ኑሮውን ሙሉ በሙሉ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በማድረግ “ሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር” በማቋቋም የራሱን የግል ስራ እየሠራ ይገኛል፡፡

ባለትዳር እና የ4 ልጆች አባት ነዉ፡፡

ወጣት አብዱልቃድር መኮ ከ1ኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርቱን በቦንጋ ከተማ ነው የተማረው፡፡

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ከሚገኝ ቤተሰብ በመገኘቱና ወላጅ አባቱ ፖሊስና የመንግሥት ተቀጣሪና በየወሩ ከመንግሥት በሚከፈተው የወር ደመወዝ ቤተሰብን የሚያስተዳድሩ ወላጅ አባቱ በአንድ ወቅት በመታሰራቸው ምክንያት ወላጅ እናቱ ይህንን የቤተሰብ ችግር ለመቀየር በሚል እሳቤ ወደ እንጀራ መጋገር ሲገቡ የዛሬው ሀኢቲ ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር መስራችና ሰብሳቢ ወጣት አብዱልቃድር መኮ ትምህርቱን በ12ኛ ክፍል በመግታት እናቱ የምትጋራበትን እንጀራ በማዟዟር የሚሸጥ እንደነበረ እና ስራውን በጣም ከትንሽ ነገር መጀመሩ ገልጿል፡፡

በቦንጋ ከተማ የሀኢቲ ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ማህበር ከመመስረቱ በፊት በተለያዩ ቦታዎች በግል ስራ ተቀጠሩ፡፡

በአንድ ወቅት አንድት ሴት እንጀራ በመጋጋር ስራ ውጤታማ መሆኗን መስማቱ ለዚህ ለአሁኑ ስራ እንዳናሳሰው በመግለፅ እንጀራና ዳቦ ጋግራው በመሸጥ የራሳቸውንም ይሁን የቤተሰባቸውን ኑሮ የተሻለ ለማድረግ የግል ስራ ለመስራት ወሰነ፡፡

በማህበር ተደራጅቶ በመሥራት ውጤታማ ከመሆኑም ባሻገር ለበርካታ ዜጎች ሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን በቦንጋ ከተማ የሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብዱልቃድር መኮ ይገልጻል፡፡

ሀኢቲ ዳቦና እንጀራ አምራች እና አከፋፋይ ማህበር መስራችና ሰብሳቢ ወጣት አብዱልቃድር መኮ(ማሙሽ) ገለጻ ማህበሩ በርካታ ችግሮችን ተሻግረው የተሻለ ዉጤት ማስመዝገቡን ገልጿል።

የማህበሩ ስያሜ በከፊኛ ሀኢቲ ሲሆን ትርጉሙ ታጋሽ ወይም ቻይ ማለት እንደሆነ በማስረዳት ወጣቶች ፈተናዎችን እንደ እድል በመቀየር የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ አለባቸዉ ብለዋል።

ሀኢት ዳቦና እንጀራ አምራቾችና አከፋፋይ ማህበር በ2008 ዓ.ም ተደራጅተው በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ 20 ሺህ ቆጥበው 200 መቶ ሺህ ብድር አገኝተው በቦንጋ ከተማ በሁለት አባላት እና በአራት ሠራተኞች ሥራ መጀመሩን የማህበሩ ሰብሳቢ ወጣት አብዱልቃድር መኮ ይናገራል፡፡

ማህበሩ በመጀመሪያ ስራ ለመጀመር ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ለማግኘት የብድር ማስያዣ አጥተው የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ዋስ በመሆን የብድር አገልግሎት ተመቻችቶ ሥራ መጀመሩን ይገልጸዋል፡፡

እንደ ወጣት አብዱልቃድር መኮ ገለጻ ከዚህ በፊት በዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ሥራ የጀመረው ማህበሩ በአሁን ላይም የኬክና ኩኪስ እንዲሁም ካፌና ሬስቶራንት ጨምሮ በኦንላይን አገልግሎት የሚሰጡ 11 ቅርንጫፎች በቦንጋ ከተማ ከፍቶ በመሥራት ውጤታማ እየሆነ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ማህበሩ በአሁኑ ሰዓት ለ136 በላይ ሥራ አጥ ዜጎች ማህበሩ በውስጡ አቅፎ እየሰራ እና ለነዚህ በጊዜያዊ ተቀጥሮ እየሰሩ ላሉ ሠራተኞች በዝቅተኛ ከ600 እስከ 30 ሺህ ብር የሚደርስ ከፍተኛ ደመወዝ እየተከፈለላቸው እንደሆነ ገልጿል።

ቀደም ሲል ሥራ በሚጀምርበት ወቅት ከመንግስት የወሰዱትን ዕዳቸውን ከፍለው መጨረሳቸውን፣ ማህበሩ ሞዴልና ውጤታማ እየሆነ በመምጣቱ በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን አውስተዋል ፡፡

ሀኢቲ ዳቦና እንጀራ አምራችና አከፋፋይ ቅርንጫፉን ከ1 የጀመረው በአሁን አገልግሎት የሚሰጡ ወደ 11 ቅርንጫፎች በማድረስ ካፒታሉን ወደ 25 ሚሊየን ብር ማድረስ መቻሉን የጠቀሱት አቶ አብዱልቃድር በቀጣይ በዚህ ዘርፍ በጣም ውጤታማ ሆኖ ተደራሽነቱን በማስፋት እንጀራን እስከ ዉጭ ሀገር ለመላክ አቅደው እየሠራ ይገኛል፡፡

ማህበሩ ከማምረቻና ማከፋፈያ ቅርንጫፍ ውጪ የራሱ ቦታ አገኝተው ደረጃውን የጠበቀው ህንፃ በቦንጋ ከተማ ገንብቶ በከተማው ያለውን የሆቴልና መዝናኛ አገልግሎት ችግርን ለማቃላል እንግዳ ማረፊያ በመስራት ራሳቸውንና በርካታ የሥራ አጥ ዜጎችንም ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችላቸውን ሥራ እየሰራ ነው

ለዚህም ባቀረቡት የቤት የመሥሪያ ቦታ ጥያቄ መሠረት ከመንግሥት በተሰጠ 4 ሺህ ካሬ ቦታ ላይ G+6 ፎቅ ለመገንባት ስራ የተጀመረ መሆኑን በመናገር ፎቁ ሲጠናቀቅ በአንድ ቀን 6 ትላልቅ ክልላዊ ጉባኤዎችን ለማካሄድ የሚያስችል እና ከ1 መቶ 20 በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊ ዜጎች ስራ እድል እንደሚፈጥር አቶ አብዱልቃድር መኮ ገልጿል።

የእንግዳ ማረፊያ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ 200 ሚሊየን የሚፈጅ ሲሆን ግንባታው አሁን ላይ 30 ከመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በሀገራች ኢትዮጵያ የተፈጠረዉን ኑሮ ዉድነት ለመቀነስና በገበያ ላይ ያለውን የጤፍ እና የስንዴ ዋጋ ለማረጋጋት ማህባሩ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት እና ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የእንሰት መጭመቅያ ማሽን በማምጣት ዳቦና እንጀራ በማዘጋጀት ለአካባቢያዉና ለአለም ገበያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅት ስራ መጠናቀቁን ወጣት አብዱልቃድር መኮ አስረድቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *