



ከአምስቱ የእስልምና መሠረቶች አንዱ የሆነዉ የኢድ አልፈጥር በዓል በመላው አለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር ታላቅ በዓል ነው፡፡
በዓሉም ከአንድ ወር የረመዳን ጾም ማብቂያን ተከትሎ በድምቀት የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም በሂጅራ አቆጣጠር ለ1 ሺህ 4 መቶ 45ኛ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል፡፡
ከእነዚህም በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ተገኝተን ያነጋገርናቸዉ የእምነቱ ተከታዮች በሰጡት አስተያየት ያለፈው የጾም ወቅት በሀይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት መልካም ተግባራትን የተከናወኑበት መሆኑን ገልጸው የኢድ ዉሎም አስደሳች እንደነበር ተናግረዋል፡፡
መልካምነት በእምነቱ አስተምህሮ ማብቂያ የለውም ያሉት የእምነቱ ተከታይ አቶ ተማም አሊ ለተቸሩ ወገኖች መድረስና የመደጋገፍ ባህላችን ተጠናክሮ ልቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
ያለፈውን ሬመዳን ወር ከፈጣሪ ይቅርታንና ምህረትን በመጠየቅ አላህ የሚወደውን የበጎነት ተግባር ሲንከውን የሰነበትንበት ነበር ያሉት ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ዶ/ር አህመድ እስማኤል ናቸው፡፡
ለአንድ ወር ሲከናወን የቆየው የረመዳን ጾም ጸሎት ዘካና ሰደቃን የመሳሰሉ መልካም ተግባራትን ፈጣሪያቸው እንዲቀበል የሚያስችል የምስጋና ጊዜ ያሳለፉት መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎች ለዚህ ታላቅ ቀን በመድረሳቸው ለሁሉም መልካም ምኞታቸዉን ገልጸዋል፡፡
የተጀመረው አቅመ ደካሞችን የመደገፍና የተለመደው መልካም ጉርብትና እንድጎለብት ሁሉም ለሰላም በሰላምና በፍቅር መኖር እንዲችል ሁሉም የደርሻቸውን መወጣት እንዳለበትም ምዕመናኑ ጠይቀዋል ሲል ደሬቴድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
