Trendings

‎የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የፈተና ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

Spread the love

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የመጀመሪያ ዙር የኦንላይን ፈተና አሰጣጥ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የፈተና ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎የቢሮው ምክትል ሀላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ሀላፊ ደስታ ገነሜ(ዶ/ር) እንደገለፁት በክልሉ በ18 ፈተና ማዕከላት 17,458 ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

‎ፈተናው በስድስት ዙር በ18 ማዕከላት እንደሚሰጥ የገለፁት ምክትል ሀላፊው 14 ማዕከላት ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ብቻ የሚሰጡ መሆኑን በመጠቆም ቀሪዎቹ 4 ማዕከላት በወረቀትና በኦንላይን እንደሚፈትኑ ጠቁመዋል።

‎በ11 ማዕከላት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የተሰጠው የመጀመሪያ ዙር ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ገልፀው በመጀመሪያ ዙር ፈተና 1261 ተማሪዎች ፈተናውን በስኬት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

‎መንግስት የፈተና አስተዳደር ስርዓትን ለማዘመን በጀመረው ሪፎርም መሰረት የኦንላይን ፈተና አሰጣጥ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ደስታ በተለይ ሂደቱን ለማሳለጥ የኢትዮ ቴሌኮሚና የመብራት ሀይል አገልግሎት የሚያደርጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ ተጠናክሮ እንድቀጥል ጠይቀዋል።

‎የፈተናውን ሂደት የተሳካ ለማድረግ ፈታኝ መምህራን የአይሲቲ ባለሙያዎች ሱቨርቫይዘሮችና የፀጥታ አካላት የሚያደርጉት የተቀናጀ ተግባራት የሚመሰገን እንደሆነም ገልፀዋል። በቀጣይ 5 ዙር የሚሰጠው የፈተና ሂደት ስኬታማና ሰላማዊ ሆኖ እንድቀጥል አሁንም ሀላፊነታቸውን አጠናክሮ እንድያስቀጥሉ ጠይቀዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *