ለብልጽግና ፓርቲ ያለውን የማይናወጥ ድጋፍ ያረጋገጠ ደማቅ ህዝባዊ ሰልፍ በህብረ-ብሔራዊቷ ቴፒ!

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሸካ ዞን፤ በህብረ-ብሔራዊቷ ከተማ ቴፒ ሕዝቡ ለብልጽግና ፓርቲ ያለውን የማይናወጥ ድጋፍና ህዝባዊ እውቅና ያረጋገጠ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍና የይምረጡን ምርጫ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ ደጋፊዎችና አባላት በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በተለያዩ ኩነቶች የደመቀው ብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍና ምርጫውን የይምረጡን ቅስቀሳ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ፤ ፓርቲው ለጀመራቸው የሰላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ያለውን ጽኑ አጋርነት በግልጽ የሚያሳይ ነው።

ሰልፈኞቹ ብልጽግና ምርጫችን ነው፣ብልጽግና እንመርጣለን ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው፣ብልጽግናን መምረጥ ሀገርን ማጽናት ነው፣በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ብልጽግናን እንመርጣለን፣ብልጽግናን መምረጥ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን መገንባት ነው የሚሉ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *