







በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ በፕሮግራም በጀት አሰራርና አተገባበር ዙሪያ በክልሉ በሚገኙ ለዘርፉ አመራሮች የተዘጋጀዉ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
የስልጠናው ዓላማ የፕሮግራም በጀት አሰራርና አተገባበር፣ ክትትልና ሪፖርትን ለመለካት የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት ላይ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ተብሏል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ከዚህ በፊት የነበሩ የበጀት ስርዓት አተገባበር ማሻሻያ በማድረግና የተለያዪ አካባቢዎችን ተሞክሮ በመቀመር በክልሉ የፕሮግራም በጀት አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለፕሮግራም የሚበጀተው ውስን ሀብት ወጪን በቀነሰ እና ገቢን መሠረት ባደረገ መልኩ እንዲተገበር ሁሉም ተቋማት ህግን መሰረት አድርው እንዲሠሩ በማስገንዘብ የፕሮግራም በጀት አሰራር ስዓቱን በየተቋማት ተግባራዊ በማድረግ ስራዎችን በውጤት ለመለካት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም አስረድተዋል።
በመድረኩም በፕሮግራም በጀት አዘገጃጀት እና አተገባበር ላይ በቢሮው ምክትል ኃላፊና የፊስካል ፖሊስና መንግስት ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለሰ ኡሮ በፕሮግራም በጀት ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በካሳሁን አሰፋ
