የቦንጋ ከተማ ለትውል ምቹ እንዲትሆን ወቅቱን የሚመጥን የከተማ ፕላን ያስፈልጋታል፦የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ

Spread the love

የቦንጋ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ላይ ያተኮረ የመረጃ ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ቦንጋ ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ መሆኗን ተናግረዋል።

ይህን የሚመጥን የከተማ መዋቅር በማስፈለጉ ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ጋር ስምምነት ተደርጎ ወደ ትግበራ መገባቱንም ጠቁመዋል።

የዛሬው መድረክ መረጃ የማሰባሰብ የመጀመሪያዉ ዙር መድረክ መሆኑን አብራርተዋል።

የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተክለአብ ቡሎ(ዶ/ር) የቦንጋ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ከነዋሪዎች መረጃ መሰብሰብ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ መዋቅሮችን በማሳተፍ ውጤታማነቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

የመደረኩ ተሳታፊዎች የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት በመወጣት ለቦንጋ ከተማ ዕድገት አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የተወጣጡ 16 አባላት ያሉት ቡድን የቦንጋ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ለማሻሻል የተጀመረ ጥናታዊ ጹሁፍ እየቀረበ ይገኛል ሲል ቦንጋ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *