




ወ/ሮ አባይነሽ ጥላሁን እና ወጣት የአብስራ አይመሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ሲሆኑ የኮሪደር ልማት እሳቤ ሲመጣ ቤቶቻቸውን የሚጎዳና ችግር የሚያስከትል ሆኖ እንደተሰማቸው አውስተው አሁን ላይ በተሰራው ስራ ‘እንኳንም መጣልን’ አልን ማለታቸው ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማት ስራው ህፃናት፣ ሽማግሌዎችና አቅመ ደካሞች እንደልብ የሚመላለሱበት እየሆነ ይገኛል ያሉት ነዋሪዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውንም ምቹ ማድረጉን አስረድተዋል።
ቀደም ሲል መኪና፣ ሞተርና እግረኛ ሁሉም አንድ ላይ እየተጋፋ የሚንቀሳቀስበት በመሆኑ የአደጋ ክስተት ሲያጋጥም እንደነበር አውስተው አሁን ላይ ሁሉም ለራሱ በተሰራው መንገድ እየተጓዘ በመሆኑ አደጋዎች መቀነሳቸውን የተናገረው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት ታምሩ ነው።
የመኖሪያ ቤቶችና የተለያዩ ድርጅቶች በስታንዳርድ እየተገነቡ በመሆናቸው ከተማዋ ውብና ማራኪ እየሆነች እንደሚትገኝ ያስረዱት ነዋሪዎቹ ስራው ተጠናክሮ ወደ ሌሎችም ሰፈሮች ሊስፋፋ ይገባል ብለዋል።
የተጀመረው የህብረተሰብ ተሳትፎን አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የተሰራውን በመጠበቅ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አመላክተው ሌሎችም የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማቱ የተጀመረባቸዉ ቦታዎች ለከተማው ተደማሪ ውበት እየሆኑ መምጣታቸውን በመጥቀስ የተጀመረዉ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ነው።
