የፓርቲውን መንትያ ግቦችን ለማሳካት አባሉ የመሪነት ሚናውን በቁርጠኝነት ሊወጣ ይገባል ፦ አቶ ሳምሶን መለሰ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የቦንጋ ብዝኃ ማዕከል የአስተዳደር ዘርፍ ብልፅግና ህብረት 2018 ዓም 3ኛ ዙር መደበኛ የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለጹት ባለፉት ወራት በፓርቲው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በተደረገው ጥረት ተጨባጭና ተስፋ ሰጭ ውጤቶች መመዝገቡ ተገልጿል።

በፓርቲው እሳቤዎች በኢኮኖሚ፣በማህበራዊና በፖለቲካ መስኮች አበረታች ውጤቶ መመዝገቡን አንስተዋል።

የፓርቲው ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር የብልጽግና ቤተሰብና ህብረት ውጤታማና ጠንካራ መሠረት የሚጥል ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

የፓርቲውን እሳቤዎች እና የታቀዱ ዕቅዶችን ለማሳካት አመራርና አባሉ ከወትሮው በተለየ አኳኋን በትብብር እና በአንድነት መስራት ይጠበቃል ያሉት አቶ ሳምሶን በዚህም አመራሩና አባሉ የለውጡን ስኬቶች፣ ድሎችና ተግዳሮቶችን በውል በመገንዘብ የሀገራችን የብልጽግና ራዕይ ለማሳካት መጠነ ሰፊ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሀዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለውና በብልጽግና ፓርቲ አብላጫ ድምጽ እንዲጠናቀቅ አባሉ እና አመራሩ የመሪነት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር አባሉ በተሰማራበት የስራ መስክ ብልጽግና ራዕይ፣ ዓላማ ፣ እሴት፣ አሻጋራ ሀሳቦችን የዕለት ተዕለት ተግባር በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ብርቱ ትግል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ባለፉት ስምንት ዓመታት በፓርቲው መሪነት የተመዘገቡ ድሎችና ስኬቶች ለማጠልሽት ሌት ተቀን የሚታትሩ እኩይ ዓላማ የላቸው ኃለይሎችን አስተሳሰባቸውንና ድርጊታቸውን መመከት እንደሚገባ ጠቅሰው የህዝብን እርካታ በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ትኩረት እንዲደረግበት አስገንዝበዋል

አባሉ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር ግንባር ቀደም የአርአያነት እሳቤዎችን በመላበስ ስሁት መረጃዎቹን በወቅቱ በማረም የሀገራችንን በጎ ገጽታ በማስተዋወቅ ፣ በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን በማጉላት፣ የፓርቲው እሳቤዎች የሀሳብና የትርክት የበላይነት እንዲይዙ ማስቻል ከሁሉም አመራርና አባል ይጠበቃል ብለዋል።

የእጩ ጊዜ የጨረሱ አባላት ወደ ሙሉ አባልነት እንዲቀላቀሉ፤ በህብረት አደረጃጀት ውስጥ በተለያየ ምክንያት የተጓደሉ አመራሮችን የሚተካ አመራር በኮንፈረንሱ ቀርቦ ፀድቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *