




የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ር/መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የካፋ ዞን ጊምቦ፣አዲዮና ቦንጋ ከተማ መዋቅሮች ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አፈጻጸም ገምግሟል ።
ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በማስተሳሰር አመራሩ በቁርጠኝነት ውጤታማ ስራ መስራት እንዳለበት የተናገሩት አቶ ማስረሻ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የመንግስት ልማት ስራዎች ውጤታማነት ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል ።
የክልሉ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ እንዲሆን አመራሩ ድርብ ተልዕኮው እንዳለበት ገልጸው ከምርጫ ስራዎች በተጨማሪ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል ።
የምርጫ ምዝገባ ስራውን በቀሪ አጭር ጊዜያት ማጠናቀቅ እንደሚገባ ገልፀው የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት በመንግሥትና በፓርቲ አመራሮች መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር እየሰሩ ያሉ አካላትን ለህዝብ ትክክለኛ መረጃ ማድረስ ያስፈልጋል ብለዋል።
የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ታዓማኒ እና ፍትሐዊ እንዲሆን ከአመራርና ባለድርሻ አካላት ጋር የአፈጻጸም ግምገማ በማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
የካፋ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ሀይሌ በበኩላቸው የምርጫ ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ከአደረጃጀቶችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
አመራሩ የመንግስትና የፓርቲ ኢንሼቲቮችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ከመፈፀም ጎን ለጎን 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲካሄድ በየደረጃው የሚገኙ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ በአግባቡ እንዲወጡ ከክልል ደጋፊ አመራሮች ሀሳብ ተነስቷል ።
የምርጫ ምዝገባ ስራዎችን በቀሪ ጊዜያት በማጠናቀቅ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል እንደሚገባና ከምርጫ ስራችን ጎን ለጎን የፓርቲ ኢንሼቲቮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አክለዋል ።
የመንግስትና የፓርቲ ኢንሼቲቮች፣ 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫና የመራጮች ምዝገባ ዙሪያ የመከረው መድረኩ ተግባራት በተያዘላቸው ጊዜያት እንዲፈፀሙ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቋል።
