በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን እውን ለማድረግ ዝግጁ ነን፡- የካፋ ዞን አርሶ አደሮች

Spread the love

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የካፋ ዞን አርሶ አደሮች ገልፀዋል።

በዞኑ ጊምቦ ወረዳ የሾምባ ሼካ ቀበሌ አርሶ አደሮች እንደገለጹት የሚመራቸውን ዕጩ ለመምረጥ የሚያስላቸውን የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውን ለኢቢሲ ተናግረዋል።

ያለፉት 6 ተከታታይ የምርጫ ሂደቶች ተሳትፈው የሚበጃቸውን የፖለቲካ ፓርቲ መርጠናል ያሉት አርሶ አደሮቹ የዘንድሮው ምርጫ ካለፉት ጊዜያት መሻሻሎች የታዩበት ነው ብለዋል።

የምርጫ ጣቢያዎች በአቅራቢያቸው መደራጀት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሀሳባቸውን በነጻነት ማንሸራሸር መቻል እና መራጩም ለውሳኔው ተገቢ መረጃዎችን ማግኘት የሚችልበት እድል መፈጠሩ ከታዘቡት ለውጦች የሚጠቀስ መሆኑን አመላክተዋል።

ሂደቱም ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የመራጮች ምዝገባ ሂደት በዞኑ ሁሉም አካቢዎች በተደራጁ የምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመቅረብ እና ምርጫዬ በተሰኘ መተግበሪያ አማካኝነት እየተከናወነ ይገኛል።

ዜጎች የመራጮች ምዝገባ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ካርድ በመውሰድ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ሊጠቀሙ እንደሚገባ አስተያየት ሰጪዎቹ አስገንዝበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *