




7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በማስመልከት ብልፅግና ፓርቲውን የሚደግፍ እና ይምረጡን የምርጫ ቅስቀሳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሸካ ዞን፤ በህብረ-ብሔራዊቷ ቴፒ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በክልሉ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሁሉም ረገድ በቂ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር ያዘጋጃቸውን ፕሮግራሞችና ራዕዮች በሰፊው ለሕዝብ በማቅረብ ድጋፍና እምነት እያገኙ ነው።
በህብረ-ብሔራዊቷ በቴፒ ከተማ እየተካሄደ ባለው የድጋፍና የቅስቀሳ ሰልፍ፤ ሕዝቡ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ያስመዘገባቸው ውጤቶች በህዝቡ ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት እንዳገኘ በግልፅ እየመሰከረ ነው።
ሰልፈኞቹ፣ የተመዘገቡት ስኬቶች ወደ ኋላ እንዳይቀለበሱ እና በቀጣይም በብልጽግና ጉዞ አብረው ለመጓዝ ያላቸውን ቁርጠኝነት በከፍተኛ መነሳሳት እየገለፁ ነው።
በዚህም ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን እምነት በተያዙት በተለያዩ መፈክሮች በማይናወጥ ድጋፍና ህዝባዊ እውቅና እያረጋገጡ ናቸው።
በመርሃ ግብሩም የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ
