የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተመካካሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ በፌዴራል ደረጃ እንዲሁም በዲያስፖራው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ወኪሎች ከየባለድርሻ አካላቱ ሲያስመርጥ መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም መሰራት የተወከሉት ተመካካሪዎች በተዘጋጀላቸው ማረፊያ ቦታዎች እየገቡ የሚገኙ ሲሆን በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ተመካካሪዎች እጅግ መሠረታዊ በሆኑ እና በተለዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ በጋራ ለመምከር ዕድሉን…
