የሸካ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

Spread the love

ምክርቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው መጠን የህዝብ ልማት ፣ ሰላምና የመልካም አሰተዳደር ችግሮች መፈታታቸው ክትትል ያደርጋሉ ያሉት የሸካ ዞን ምክር ቤት ዋና አፌ -ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ምክር ቤቱ በ2015 በጀት ዓመት በሰክተሮች ክትትል እና ቁጥጥር ስራን በማጠናከር የተግባር አፈፃፀም ዉጤታማ እንዲሆን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በዞኑ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት መከናወኑን ገልፀዉ ከግብርና አኳያ በኩታገጠም እርሻ ፣የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች የተሻለ አፈፃፀም ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የፍትህ ስርአቱን ስርዐቱን ከማሳለጥ አኳያ የታዩ ጥሩ ተግባራት አፈፀፀም ተጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል ።

ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃር የመድሐኒት ግዥ አቅርቦት ፣በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ቀጣይ ትኩረት እንደምሻ ገልፀዋል ።

የ2015 በጀት ዓመት የዞን አስተዳደር እና የፍርድ ቤቶች የማጠቃለያ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ይደረግበታል ።

ለሁለት ተከታታይ ቀን በሚቆየው ጉባኤ የተለያዩ ደንቦች የ2016 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድና በጀት ጨምሮ ሹመት ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የሸካ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *