


በቦንጋ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ት/ቤቶች የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ በይፋ ተጀምሯል።
ምዝገባ ላይ እያሉ ያነጋገርናቸው የቢሻው ወ/ዮሐንስ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት ተማርዎች ዛሬ በይፋ በጀመረው ምዝገባ ዕለተ በመገኘታቸው መደሰታቸዉን ገልፆ በመስከረም 03/2016ዓ.ም በሚጀምረው መደበኛ ትምህርት በነቃ ሁኔታ ትምህርታቸውን እንደሚጀምሩም ተናግረዋል::
ወላጆቻቸዉም በበኩላቸው የትምህርት ጉዳይ የትምህርት አካላት ብቻ ሳይሆን የወላጆችንም ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ ተማሪዎችን ወደ ት/ቤት መላክም ሆነ የትምህርት ቁሳቁስ በሟማላት የበኩላቸውን ድርሻ እንደምወጡ ተናግራዋል::
የቢሻው ወ/ዮሐንስ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት መምህራን በበኩላቸው በወቅቱ ምዝገባ መጀመሩ የዓመቱን ትምህርት ሥራ በተቀመጠው የትምህርት ካላንደር ለማጠናቀቅ ሚናዉ የጎላ መሆኑን ተናግረው መስከረም 3 ለሚጀመረው መደበኛ ትምህርት ዝግጅት ላይ መሆናቸዉን አብራርተዋል::
በሌላ በኩል ተማሪዎችን በጊዜ ተቀብሎ ማስተማር ከዚህ በፊት በዋናነት ችግር ሆኖ ስነሳ ለነበረው ለትምህርት ጥራት መፍትሄ ሊሆን እንደምችልም ገልፅዋል::
የት/ቤቱ ዋና ርዕሰ መምህር ተክሌ አለማየሁ ምዝገባ በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን ተናግረው የተጀመረውን ምዝገባ በዚህ ልክ በማሰቀጠል ከተቀመጠው ጊዜ ወዲህ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ በዞን ደረጃ በሁሉም ት/ቤቶች ምዝገባ ዛሬ በይፋ መጀመሩን ተናግረው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተማሪ በወቅቱ ቀርበዉ ተመዝግበዉ ወቅቱን በጠበቀ ሁኔታ ትምህርት በመስከረም 3 መጀመር ይገባል ብሏል::
አቶ ተፈሪ አክለዉም ማነኛዉም ዕድሜዉ ለትምህርት የደረሰ ልጅ ወደ ትምህርት እንድገባ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በአጠቃላይ በዞን ውስጥ ካሉ 6 መቶ 29 ትምህርት ቤቶች የ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት ስራ ለመጀመር በተደረገው ቅድመ ዝግጅት ከነሐሴ 22/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3/2015 ዓ.ም ድረስ 3 መቶ 15 ሺህ 6 መቶ 78 መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ በማካሄድ የመማር ማስተማሩ ስራ መስከረም 3/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚጀመር መሆኑንም አቶ ተፈሪ ተናግሯል።
በመጨረሻም የትምህርት አመራር፣ የሱፐርቫይዘሮች፣ ርዕሰ-መምህራንና የትምህርት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ ወላጆች እንድሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተጀመረዉን ምዝገባ በተያዘዉ ጊዜ እንድጠናቀቅ ድርሻቸውን እንድ ወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል ሲል ካፋ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
