ጉርጉቶ /የእግዜር ድልድይ

Spread the love

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ከካፋ ዞን ከቦንጋ ከተማ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወደ ጠሎ ወረዳ በሚወስደው መንገድ ከማኪራ ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ቡናና ደን በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል።

ፈፅሞ የሰው የእጅ ፈጠራና ልፋት ሳይዳስሰው በተፈጥሮ በፈጣሪ ጥበብ የተሰራ ድንቅ ድልድይ ነው። ጉርጉቶ የእግዜር ድልድይ!

ይህንን ድንቅ የቱሪስት መስህብ በየአመቱ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኚዎች ይጎበኙታል።

በስሩ ለጉማ ወንዝ የሚገብር ትልቅ ጅረት የሚያልፍ ሲሆን በላዩ ወደ ዴቻ ወረዳ የተለያዩ መንደሮችና ቀበሌዎች ሰዎችና ከብቶች በየቀኑ ይመላለሱበታል በዚህ ድንቅ የተፈጥሮ ድልድይ ጉርጉቶ።

አካባቢው በውብ የደን ክልል የተከበበ በመሆኑ በበጋና ክረምት ሁሌ ታላቅ ግርምትን የተጎናፀፈ ግርማ ሞገስን ሰጥቶታል፤ለጉርጉቶ የእግዜር ድልድይ።

ይሄንን የተፈጥሮ መስህብ ይበልጥ ለጎብኚዎች ምቹ ለማድረግ በዞኑ አስተዳደር የተለያዩ የመንገድ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *